በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድርቅና ጤና - ረሃብ በሽታ ነው


ኤል ኒኞ
ኤል ኒኞ

“ድርቅ የሚያስከትለው የበረታ ረሃብ እራሱ በሽታ ነው” ይላሉ የሥነ-ምግብ ጤና ባለሙያዎች፡፡ የአካልና የአዕምሮ ጤና ጉዳቶችን ያስከትላል። በሕፃናት ላይ በዕድሜ ዘመን ሙሉ የማይሽር የዕድገት መቀጨጭን ያመጣል።

የዘንድሮው ኤል ኒኞ ያስከተለው ድርቅ ብርታትና ስፋት ባለፈው ግማሽ ምዕት ዓመት ታየቶ እንደማይታወቅ ተነግሯል።

“ድርቅ የሚያስከትለው የበረታ ረሃብ እራሱ በሽታ ነው” ይላሉ የሥነ-ምግብ ጤና ባለሙያዎች፡፡ የአካልና የአዕምሮ ጤና ጉዳቶችን ያስከትላል። በሕፃናት ላይ በዕድሜ ዘመን ሙሉ የማይሽር የዕድገት መቀጨጭን ያመጣል።

ተኀዋስያንና ተውሣኮች ፈጥነው ለመራባት ዕድል ስለሚያገኙ የገፀ-ምድሩንም ሆነ የከርሰ-ምድሩን ውኃ ስለሚበክሉት ያለው ውኃም ቢሆን ተገቢው ጥንቃቄና ክትትል ካልተደረገበት ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።

የኤል ኒኞ ክስተት
የኤል ኒኞ ክስተት

በምግብ የተጎዳ አካል አጣዳፊ በሆኑ የመተንፈሻ አካላትና የምግብ ሥርዓት አካላት በቀላሉ ይጎዳሉ።

ቁጥራቸው የበዛ ተላላፊ በሽታዎችም ለመሠራጨት ዕድል ያገኛሉ።

በተለይ የድርቁ ወቅት ወደማለፉ ሲጠጋ ወይም በመሃሉ የሚገኙ የዝናብ አጋጣሚዎችም ከፀጋቸው ጋር ብዙ የማኅበረሰብ ጤና እክሎችንም እንደሚያስከትሉ ይታወቃል፡፡

ሰሞኑን ዝናብ እየጣለ ነው።

የኢትዮጵያ ሚቲኦሮሎጂ ኤጀንሲ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዱላ ሻንቆና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኅብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ማዕከል ኤክስፐርት አቶ ጌታነህ አብረሃ የሰጡን ማብራሪያዎች የወቅቱን ሁኔታና ዝግጁነትና ምላሹን ይጠቁማሉ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ድርቅና ጤና - ረሃብ በሽታ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:21:22 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG