“ጠዋት ቂሊንጦ ስንሄድ አራቱ ሰዎች የሉም። ያሉበትን የሚነግረን አላገኘንም።” ወ/ሮ ዓይናለም ደበሎ፤ ላለፉት አራት ወራት በማዕከላዊ እሥር ቤት የነበሩትና ካለፈው አርብ አንስቶ ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ተዛውረዋል፤ ከተባሉት የኦሮሞ ፌድራሊስት አመራር አባላት ቤተሰብ አባላት አንዷ ናቸው።
በኦሮሚያ ክልል አልፎ አልፎ በተማሪዎችና በነዋሪዎች የሚካሄደዉ ተቃዉሞና የጸጥታ ሃይሎች የሃይል እርምጃ ምላሽም ቀጥሏል። በጉጂ ዞን ኦዶሻኪሶ ወረዳ መጋደር በተባለ መንደር ባለፈዉ ማክሰኞ በዳዳ ጋልቹ የሚባል ወጣት በመንግስት ሃይሎች መገደሉን የአካባቢ ነዋሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ገልጸዋል። በወረዳዉ የሻኪሶ ከተማ አስተዳዳሪዎች የወጣቱን ሕይወት ማለፍ እንደሚያዉቁ ለወንጀሉ ማን ሃላፊ እንደሆነ እንደማያዉቁ ግን ገልጸዋል።
ኦሮምያ ክልል ውስጥ በሆሮ ጉዱሩ ዞን የታሠሩ ሰዎችን እንዲያቀርብ ዳኛ የሰጠውን ትዕዛዝ ፖሊስ አልቀበልም ማለቱ ተነግሯል።
ታሣሪዎች የረሃብ አድማ እያደረጉ መሆናቸውንም ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ያስረዳሉ።
በኦሮሚያ የተነሳው ተቃውሞ አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎቸ ይናገራሉ፡፡ በአርሲና በምዕራብ ወለጋ ዞን ተማሪዎችና ነዋሪዎች እየታሠሩና ድብደባ እየተፈጸመባቸው እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ባልደረቦች ጃለኔ ገመዳና ነሞ ዳንዲ ያጠናቀሩትን ዘገባ ጽዮን ግርማ ታቀርበዋለች፡፡
ሕዳር ሁለት ቀን የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሏል። በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች፤ ዞኖችና ወረዳዎች ተቃውሞው ስለመቀጠሉ የአካባቢው ነዋሪዎች አስተያየት ሲሰጡ ይደመጣል። ዛሬም ሰዎች ይሞታሉ፣ይታሠራሉ እንዲሁም ይደበደባሉ የሚሉ አስተያየቶች ይነገራሉ። የዘገባዎቹን ዝርዝር ጽዮን ግርማ ይዛለች።
በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች ዛሬም የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች እንደነበሩና በአንዳንድ አካባቢዎች ግጭትም መስተዋሉ ተሰምቷል፡፡
በአምቦ እስር ቤት ተቃጥሏል፤አንድ የዘጠኝ ዓመት አዳጊ ተገድሏል
ኦሮምያ ውስጥ በምሥራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ አካባቢዎች ሰሞኑን የታየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዛሬም ቀጥሎ በተለይ በምሥራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።
ምዕራብ አርሲ ውስጥም ከከትናንት በስተያ አንስቶ ግጭቶች መኖራቸው ተሰምቷል።
የአፋን ኦሮሞ ዝግጅት ክፍላችን ባልደረቦች ጃለኔ ገመዳ፣ ቱጁቤ ኩሳና ነሞ ዳንዲ ወደ ተለያዩ ከተሞች ደውለው ያጠናቀሯቸው ዘገባዎች አሉ። ሰሎሞን ክፍሌ ያጠናቀራቸው ዝርዝሮች።
የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ ላለፉት ሁለት ወራት በላይ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ እንደቀጠለ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ።
ከሁለት ወራት በላይ ያስቆጠረው የተቀሰቀሰው የተቃውሞ እንቀስቃሴ፣ ዛሬም በአንዳንድ አካባቢዎች መቀጠሉ እየተዘገበ ነው።
በሳምንቱ ማብቂያ ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ዛሬ ተቃውሞ እንደተካሄደባቸው ከተገለጹት መካከል፥ ምዕራብ ሐረርጌ ዞን ሜሦ ወረዳና ምዕራብ ሸዋ ይገኙበታል።
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል ከስምንት ሳምንታት በፊት የጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በተለያዩ ከተሞች እንደቀጠለ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።
በኦሮሚያ ክልል የአዲስ አበባንና የፊንፊኔን ልዩ ዞኖችን ለማቀናጀት የተነደፈዉን ማስተር ፕላን በመቃወም የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ትላንትና በዛሬዉ እለት በጂማና በሃሮማያ ዩኒቬርሲቲዎች ተካሂደዋል፥ የመንግስት ጸጥታ አስከባሪ ሃይሎችም ተማሪዎቹን በመደብደብ ተቃዉሞዉን መበተናቸዉ ታዉቋል።
በኦሮሚያ - ጊንጪ ከተማ ህዳር ዘጠኝ ቀን የጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ ዛሬም በምዕራብ ወለጋ ሁለት ከተሞች መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለቪኦኤ ገልፀዋል።
የኦሮሚያ የሰሞኑ ሁኔታ ያለፈው ሥርዓት ናፋቂዎችና ጠባቦች የፈጠሩት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ መግለጫ ሰጡ፡፡
በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ 11 የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ሰልፍ ተስፋፍቷል።
ሊብያ ውስጥ የሚገኙ ከአምስት መቶ ሃምሣ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያንና ኤርትራዊያን ስደተኞች ሰሃራ በረሃ ውስጥ በሚገኝ እሥር ቤት መታጎራቸውንና እንግልት እንደሚደርስባቸው በመግለፅ አማርረዋል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ