በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃዋሚዎች ጥያቄ:- ለምን የታሠሩ አይፈቱም? ለምን ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ አይከፈልም?


የተቃውሞ ሰልፎች (ከማኅበራዊ ሚድያ የተገኘ ፎቶ)

የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም በኦሮሚያ ላለፉት ሁለት ወራት በላይ እየተካሄደ ያለው እንቅስቃሴ እንደቀጠለ መሆኑን ምንጮች ይናገራሉ።

መንግሥት እቅዱ መሰረዙን ከሁለት ሳምንታት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል። ሆኖም ተቃዋሚዎች፥ ማስተር ፕላኑ ተሰረዘ መባሉ የማታለያ ዘዴ ካልሆነ በቀር ለምን የታሠሩ አይፈቱም? ለምን ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ አይከፈልም? ሲሉ ይጠይቃሉ።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የአርሦ አደሩ የመሬት ባለቤትነት መብት ይረጋገጥና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ይወገዱ የሚሉ ጥያቄዎችን ያነገቡ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ዛሬም ቀጥለው መዋላቸውን ምንጮች ይናገራሉ።

የኦሮምያ ክልል
የኦሮምያ ክልል

የአፋን ኦርሞ አገልግሎት ባልደረባ ናሞ ዳንዲ ተከታትሎ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል። ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የተቃዋሚዎች ጥያቄ፧- ለምን የታሠሩ አይፈቱም? ለምን ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ አይከፈልም?
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:10 0:00

አስተያየቶችን ይዩ (3)

XS
SM
MD
LG