ዋሽንግተን ዲሲ —
በኦሮምያ ክልል በየተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና አንዳንድ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎች፣ የአዲስ አበባንና የፊንፊኔ ዙርያ ዞኖች የማስተር ፕላን እቀድ አስመልክቶ ከሁለት ወራት በላይ ያስቆጠረው የተቃውሞ እንቀስቃሴ፣ ዛሬም በአንዳንድ አካባቢዎች መቀጠሉ እየተዘገበ ነው።
በምዕራብ ሃረርጌዋ የሜሶ ከተማ ተሰማርቷል ያሉት የፖሊስ ሃይል፣ ችግርና ተጨማሪ በደል እየፈጸመብን ነው ሲሉ አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች እየከሰሱ ናቸው።
የወረዳው ባለስልጣናት ግን ግጭቱ ካጎራባች የሶማሌ ክልል አንዳንድ ነዋሪዎች ጋር የተፈጠረ የድምበር ጉዳይ ሲሆን፣ ወደዚያው የተሰማራው የመከላከያ ሰራዊትም ግጭቱን ለማርገብ ነው ሲሉ ያስተባብላሉ።
የኦሮምኛ ክፍል ባልደረቦቻችን ናሞ ዳንዲ ሁለቱን ወገኖች አነጋግሮ ያጠናቀረውን ዘገባ አሉላ ከበደ አቅርቦታል ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።