በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍንጫአ ፖሊስ የዳኛ ትዕዛዝ ሳያከብር ቀረ


የፍንጫአ ካርታ
የፍንጫአ ካርታ

ኦሮምያ ክልል ውስጥ በሆሮ ጉዱሩ ዞን የታሠሩ ሰዎችን እንዲያቀርብ ዳኛ የሰጠውን ትዕዛዝ ፖሊስ አልቀበልም ማለቱ ተነግሯል።

ኦሮምያ ክልል ውስጥ በሆሮ ጉዱሩ ዞን የታሠሩ ሰዎችን እንዲያቀርብ ዳኛ የሰጠውን ትዕዛዝ ፖሊስ አልቀበልም ማለቱ ተነግሯል።

የተቃውሞ እንቅስቃሴውም እንደቀጠለ መሆኑን አንድ የከተማዪቱ ነዋሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

“ኦሮምያ ውስጥ ሰፊ ተቃውሞ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ የተነሣ በወረዳችን ትምህርት ቤቶች ከተዘጉ ሰንብቷል። በተለይ የፍንጨዋ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንዴ ለፈተና ገብተው ከዚያ አልተመለሱም። ሰው እየሞተ አንማርም ብለዋል። በዚህም የተነሣ የመንግሥት ኃይሎች ሰዉን ከገጠር እስከ ከተማ ሲደበድቡ ነበር። የታሠሩ ተማሪዎች፣ አስተማሪዎችና ነዋሪዎች አሉ፡፡ የታሠሩት እስከ ዛሬ ፍርድ ቤት አልቀረቡም።” ብለዋል የከተማዪቱ ነዋሪ አቶ ጋዲሳ ጅራ።

አቶ ጋዲሳ አክለውም ሰኞ ማታ፤ አሥራ አንድ ሰዓት ላይ ይዘዋቸው እንደሄዱና ወደ ሻምቡ ከተማ እንደወሰዷቸው፤ ሰዎች ከአባይ ጮመን ወረዳ ብቻ ሳይሆን ከጃርቴ፣ ከአሙሩና ከሌሎችም ወረዳዎች ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ተይዘው የት እንደተወሰዱ እንደማያውቁ አቶ ጋዲሳ ተናግረዋል።

ከታሠሩት መምህራን አንዱ የሆኑት የአቶ ሽብሩ ባለቤት ወይዘሮ ሽታዬ በቃና ለቪኦኤ ሲናገሩ “ተጠርጣሪዎቹ ስምንት ሰዓት ላይ እንዲቀርቡ የወረዳው ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሰጠ። ፖሊሶቹ በቀጠሮው ሰዓት እሥረኞቹን ሳይዙ ቀረቡ። ዳኛውም ‘የታዘዛችሁት የያዛችኋቸውን ሰዎች አምጡ ተብላችሁ ነው’ ብለው እንደገና ለዘጠኝ ሰዓት ቀጠሩ። በዚህኛው ቀጠሮ ፖሊስም እሥረኞቹም ሳይቀርቡ ቀሩ። የቀጠሮው ሰዓት ሲያልፍ እኛ ዳኛው ዘንድ ሄደን ምን እንደሆነ ጠየቅናቸው። ፍርድ ቤቱ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ ነገሩን። ቀጠሮ እንደገና ለማግስቱ ተሰጠ። ሁለት የፖሊስ አባላት መጥተው ‘ታሣሪዎቹን ማምጣት አንችልም፤ እኛ ጋ ፌደራሎች በአደራ ያስቀመጧቸው ናቸው’ አሉ። ፍርድ ቤቱም ‘በዚህ ዓይነት መዝገቡ ተዘግቷል’ ብሎ ነገረን።” ብለዋል።

የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ሽብሩ ዋቅወያ በሰጡት ቃል “የታሠሩት ሰዎች ቤተሰብ ነን ብለው አምስት የሚሆኑ ሰዎች እኛ ጋ መጥተዋል። ከዚያ ውስጥ ያጣራነው የዋስትና መብት እንዲጠበቅልን ፖሊስን ጠይቀን ነበር የዋስትና ቢፈቀድም ፖሊስ ለማቅረብ ፍቃደኛ አልሆነም የሚል ነበር። እንደ ፍርድ ቤት እነዚህ ሰዎች የት እንደተወሰዱ አናውቅም። በዞን ደረጃ ተወያይተን እንዲህ ዓይነት አቤቱታ ካለ መፍትሔ እንዲሰጥበት ሃሣብ ተለዋውጠን ነበር። ከዚያ በኋላ ጉዳዩ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ ያጣራነው ነገር የለም። የተነጋገርነውና የተስማማነው ግን የታሠረ ሰው ካለ እንዲፈታ ነበር።” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የፍንጫአ ፖሊስ የዳኛ ትዕዛዝ ሳያከብር ቀረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:47 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG