በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦፌኮ ሰልፉን አዛወረ፤ በዓለም ዙሪያ ሠልፎች ተካሂዱ


ዋሽንግተን፤ ዲ.ሲ. - ዩናይትድ ስቴትስ
ዋሽንግተን፤ ዲ.ሲ. - ዩናይትድ ስቴትስ

የኦሮሚያ የሰሞኑ ሁኔታ ያለፈው ሥርዓት ናፋቂዎችና ጠባቦች የፈጠሩት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ መግለጫ ሰጡ፡፡

ካልጋሪ-ካናዳ
ካልጋሪ-ካናዳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:13:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኦሮሚያ ክልል ውስጥ እየተወሰደ ያለው የኃይል እርምጃ እንደቀጠለ ነው ሲሉ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ፀሐፊና የመድረክ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ በቀለ ነጋ አስታወቁ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ከአዲስ አበባ ከተማ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በተነሣው ውዝግብ ሳቢያ የተወሰደውን ሕይወት ያጠፋ እርምጃ እየተቃወሙ ያሉ በርካታ የተቃውሞ ሰልፎች በበርካታ የዓለም ከተሞች ባሉ ኢትዮጵያዊያን ተካሂደዋል፡፡

ብራስልስ ላይ ሰልፍ የወጡ የአፋር ተወላጆችና ሌሎችም ሰሞኑን ከሚታየው የኦሮሚያ ሁኔታ ጋር የተያያዙና ሌሎችም ጥያቄዎችን ይዘው አደባባይ ወጥተዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ የኦሮሚያ የሰሞኑ ሁኔታ የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂዎችና ጠባቦች የፈጠሩት ነው ሲሉ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ለዝርዝር ዘገባዎች የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG