በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጅማና ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ትላንት ምሽትና ዛሬ ማለዳ ላይ የተከሰቱ ድንገቶች


e Oromo community of Ethiopia living in Malta, protest against the Ethiopian regime in Valletta, Malta, December 21, 2015.
e Oromo community of Ethiopia living in Malta, protest against the Ethiopian regime in Valletta, Malta, December 21, 2015.

ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ክልል ከስምንት ሳምንታት በፊት የጀመረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ በተለያዩ ከተሞች እንደቀጠለ መሆኑን ምንጮች ተናግረዋል።

በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ ከትናንት በስትያ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የመንግሥት ሓይሎች ርምጃ እየወሰዱ መሆኑንና ተማሪዎች ወደ አካባባቢው ማኅበረሰብ እየሸሹ መሆኑን የኦሮሚኛ ክፍል ባልደረቦቻችን ያነጋገሯቻቸው ነዋሪዎች አመልክተዋል።

ፌዴራል ፖሊስ “ልጆቹን ለምን ትሸሽጋላችሁ” በማለት አርሶ አደሮች ላይ ተኩስ መክፈቱንና የተጎዱ ሰዎች መኖራቸውን ምንጮቹ ገልጠዋል ።

ለደህንኔቱ ሲል ስሙ እንዳይገለጽበት የጠየቀ የዓይን ምስክር ስለ ሃሮማያ ዩኒቨርሲቲው ሁናቴ ለባልደረባችን ነሞ ዳንዲ እንዲህ ሲል ገልጿል።

"ተማሪዎቹ በዩኒቨርስቲው አካባቢ ወዳሉት ቀበሌዎች ሸሽተው ያገኙት ሰው ጋር ተሸሸጉ" ፌደራል ፖሊስ ደግሞ የደበቃችሁትን ተማሪ አውጡ በማለት አርሶ አደሩን መደብደብ ያዘ። “ተማሪው ለነፍሱ ብሎ እኛ ጋር መጥቶ ተደበቀ። አንተ ጋር መጥቶ የተደበቀን ሰው እንዴት አሳልፈህ ትሰጣለህ እኛም ኦሮሞዎች እነሱም ኦሮሞዎች ብሎ እምቢ አለ አርሶ አደሩ።”

የዓይን ምስክሩ ሲቀጥል፡-“መከላከያም ተኩስ ከፈተ፣ ብዙዎች በጥይት ተመትተዋል። ሁለት አርሶ አደሮች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል። አሁንም ተኩስ ይሰማል። አርሶ አደሩም ሜንጫውን ይዞ ከያለበት ለመረዳዳትና ለመመከት እየሞከረ ነው። መከላከያዎች መንገዱን በመዝጋት ላይ ስላሉ ሁኔታውን ለማወቅ ያስቸግራል የሞተም ሰው ሊኖር ይችላል” ብሉዋል።

በተመሳሳይ በሃረማያ ሁለተኛ እና መሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎችም ትናንት የተቃውሞ ሰልፍ በማድረጋቸው በዕለቱ የተያዙትን ጨምሮ ወደ 200 የሚሆኑ የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በሃሮማያ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እየተንገላቱ ናቸው ሲል አክሎ አስረድቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ወለጋ ኪራሙ ከተማ የታሰሩ ተማሪዎች እና “አቶ በቀለ ገርባ ይፈታ” ብለው የመሰናዶ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ እንዳደረጉና የአካባቢውም ማህበረሰብ ከተማሪዎቹ ጋር ተቀላቅሎ ተቃውሞ ማሰማቱን አንድ ስሙን መናገር ያልፈለገ ተማሪ ለባልደረባችን ቱጁቤ ኩሳ ገልጾላታል። “የአካባቢው ኣስተዳዳሪና የከተማዋ የኦህዴድ ተመራጭ ወይዘሮ አበባ በየነ መጥተው ለማረጋጋት ሞከሩ ። ተማሪዎቹ ግን የታሰሩት እስኪፈቱ አንማርም ብለው ተቃውሞኣቸውን ቀጥለዋል ብለዋል” ካሉ በሁዋላ፣

“በሁዋላ አጋዚ ከጊዳ አያና ከተማ መጣ ። ተማሪዎችን ለቅመው ወደእስር ቤት ወሰዱ። መምህር ገደፍ የሚባሉ አስተማሪ “ አንተ ነህ ይህን ያነሳሳኸው” ተብለው እስር ቤት ውስጥ እየተሰቃዩ ናቸው። ሴቶች ሳይቀሩ ነው እስር ቤት ተወስደው እየተደበደቡ ያሉት።” ሲሉ አመልክተዋል።

በኪራሙ ከተማ ተደረገ የተባለውን ሰልፍ በተመለከተ ለማጣራት የወረዳው አስተዳዳሪ ወደሆኑት አምሳለ ጃለታ ቢደወል ስልካቸውን አላነሱትም። በሃሮማያ ዩኒቨርስቲና አካባቢው የተደረገውን ተቃውሞ እና ተጎዱ የተባሉትን ሰዎች በሚመለከት ደግሞ ትናንት ያነጋገርናቸው የምዕራብ ሐረርጌ ፖሊስ ኮማንደር ኡስማን መሃመድ “የተባለው ሁሉ ሃሰት ነው፣ ሁሉ ሰላም ነው” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል።

በኦሮምያ የተለያዩ አካባቢዎች ከተቀሰቀሰው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ጋር ተያይዞ በጅማና የሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ትላንት ምሽትና ዛሬ ማለዳ ላይ መቀጠላቸው ሰዎች ገልጸዋል።

ድንገቶችን የተከታተሉት የኦሮምኛ ክፍል ባልደረቦቻችን ጃለኔ ገመዳና ነሞ ዳንዲ ያጠናቀሯቸው ዘገባዎች አሉ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

በጅማና የሃሮማያ ዩኒቨርሲቲዎች ትላንት ምሽትና ዛሬ ማለዳ ላይ የተከሰቱ ድንገቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:19 0:00

XS
SM
MD
LG