ትናንት ወዲያ በደቡብ ክልል ሼካ ዞን ቴፒ ከተማ ተፈጥሮ ለሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነውን የፀጥታ ችግር ወደ ሰላም ለመመልስና ህዝቡን ለማረጋጋት እየተሰራ ያለ ሥራ አለመኖሩን የከተማው ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ለቪኦኤ ገለጡ።
"ደኅንነታችን አደጋ ላይ እንዳይወድቅ" በሚል ሥጋት ውስጥ እንድንኖር የተገደድነው የክልሉና የዞን መንግሥት ወንጀለኞችን ለህግ ስለማያቀርቡ ነው” ሲሉ የደቡብ ክልል የቴፒ ከተማ ነዋሪዎች ከሰሱ።
ከሁለት ሳምንታት በፊት በባሌ ዞንጨ ተከስቶ የነበረው የአንበጣ መንጋ ወረራ በደቡብ እና ምስራቅ የኦሮምያ ክልል ዞኖች እየተስፋፋ ነው ተባለ።
“የደቡብ ሱዳን ታጣቂዎችና ቁጥራቸው አሥር ሺህ ይደርሣል የተባለ ስደተኞች የኢትዮጵያን ድንበር ዘልቀው 200 ኪሎ ሜትር ገብተዋል” ሲል የምዕራብ ኦሞ ዞን አስተዳደር አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ውሳኔ ህዝብ ቋሚ ውጤት መግለፁን ተከትሎ የሲዳማ አርነት በመግለጫ የደስታና የምስጋና መልዕክት መግለጫ አስተላለፈ። በመግለጫው ከሲዳማ ክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ሃማሌ 11/2011 ዓም በተፈጠረው የፀጥታ ችግር የታሰሩ ወጣቶች እንዲፈቱ ጠይቋል። በአቶ ዱካሌ ላሚሶ እና በዶ/ር ሚሊዮን ቱማቶ ይመራሉ በተባሉ በሁለቱ ሲአንኖች መካከል የነበረው ውዝግብም ምርጫ ባሳለፈው ውሳኔ ፍፃሜ ማግኘቱን አመልክቷል መግለጫው።
ብልፅግና ፓርቲ ህብረ - ብሄራዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ዕድል እንደሚሰጥ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ተናገሩ።
ለሲዳማ ውሳኔ ህዝብ ድምፅ ከሰጡ መራጮች ውስጥ 98 ነጥብ 5 በመቶ ሻፌታን መምረጣቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
የሲዳማ ውሳኔ ህዝብ መጠናቀቅን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ
የሲዳማ ውሳኔ ህዝብ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላይ፣ ከሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፦
የሲዳማ ውሳኔ ህዝብ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት በአለታ ወንዶ
የሲዳማ ውሳኔ ህዝብ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ መንግሥት በቂ የፀጥታ ኃይል ማሰማራቱን የሲዳማ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
ሀዋሳ ከተማ ወደ ስላሟ እየተመለሰች ነው ሲሉ የከተማዪቱ ከንቲባ አስታውቋል።
የሲዳማ ውሳኔ ህዝብ የመራጮች ምዝገባ ዛሬ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች መጀምሩን የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ አስታወቁ።
ለሲዳማ ውሳኔ ህዝብ ህዝባዊ ቅስቀሳ ዛሬ በሃዋሳ ከተማና በዞኑ ወረዳዎች ተጀመረ። ቅስቀሳውን እያካሄደ ያለው የሲዳማ ዞን መንግሥት መሆኑም ታውቋል። በአንፃሩ ግን በተቃራኒው በኩል የሚደረግ ቅስቀሳ የለም።
በኢትዮጵያ ልማዳዊ ጎጂ አድራጎቶችን ለማስቀረት ትልቅ አስተዋጸኦ ያደረጉ ዶ/ር ቦጋለች ገብሬ አረፉ።
ኢትዮጵያ አሁን ከገባችበት ቅርቃር ልትወጣ የሚትችለው በመነጋገር፥ በውይይት እንዲሁም በሚያጣሉን ታሪኮች ላይ ድርድር በመደረግ የጋራ ታሪክና አንድነትን በመፍጠር እንደሆነ ምሁራን ተናገሩ።
በኢትዮጵያዊያን መካከል እየታየ ያለው ያለመተማመን፣ የሥጋትና የጥርጣሬ መነፈስ አስወግዶ፣ ሠላምና የህዝብን አብሮነት ቀድሞ ወደነበረበት ለመመለስ የሠላም ግንባታ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ የሠላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ጉባዔ የሲዳማን ውሳኔ ህዝብ ለማስፈፀም ያስችላል የተባለውን የህግ ማዕቀፍ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
የደቡብ ክልል ምክር ቤት የህዝብ እንደራሴዎች በክልሉ ለሚነሱ የመዋቅር ጥያቄዎች የክልሉ መንግስት ምላሽ መስጠት አልቻለም ሲሉ ቅሬታቸውን አሰሙ።
የእርቀ ሰላም ኮሚሽን በደቡብ ክልል በሚያከናውነው ሰላምና እርቅ ሥራ ዙርያ ከክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ጋር ዛሬ በጽ/ቤታቸው መከሩ።ኮሚሽኑ በዚህ ወቅት እንዳለው በሕዝብ መካከል ሳይታወቅ የገነገነውን በቀል ቁርሾና ጥላቻዎችን በጥናትና በአገር በቀል እውቀት ላይ ተመስርቶ ለመፍታት የሚያስችል ስራ እየሠራ መሆኑን አስታውቋል።
ተጨማሪ ይጫኑ