በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍቼ - ጨምበላላ በዓል


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ለዘመናት በሚሊዮኖች የሚቆጠር የሲዳማ ህዝብ በሚታደምበት በጉዱማሌ አደባባይ ይከበር የነበረው የፍቼ -ጨምበላላ በዓል በኮሮና ምክንያት በሲዳማ ወረዳዎችና በሃዋሳ ከተማ ለባሰ ችግር የተጋለጡ ዜጎችን በመደገፍ እየተከበረ ነው።

የ2013ዓ.ም የፍቼ -ጨምበላላ በዓል በቤት ውስጥ እንዲከበር የሲዳማ ባህል ሸማግሌዎች በመወሰን ጥልቅ አስተዋይነታቸውና ኃላፊነታቸውን ያስመሰከሩበት መሆኑን የገለጡት የሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ለዳሞ ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት በዓሉ በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያከብሩ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አሕመድ የሲዳማ ሽምግሌዎች ዓለማችን ያለችበትን ሁኔታ በመረዳት በዓሉ በቤት እንዲከበር ያስተላለፉት ወቅታዊ መልእክት ለሀገራቸውና ለሕዝባቸው ኃላፊነት የሚሰማቸው፤ ከምንም ነገር በላይ የሰው ሕይወት የሚገዳቸው መሆኑን ያሳየ በመሆኑ አድናቀዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የፍቼ -ጨምበላላ በዓል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:07 0:00


XS
SM
MD
LG