ሀዋሳ —
የተወሰደው ናውና ውጤት ከመገለፁ በፊት ከሶማሌ ክልል ሞያሌ ዳዋ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ውስጥ የተለቀቁ 41 ተጠርጣሪዎችና በቫይረሱ የተያዘ አንድ ግለሰብ ወደ ደቡብ ክልል መገባታቸው በክልሉ ቫይረሱን የመከላከል ሂደት አሳሳቢ ማድረጉን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ርስቱ ይርዳው ተናገሩ።
ርዕሰ መስተዳደሩ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ቫይረሱ የተገኘበትን ጨምሮ ከሱ ጋር የነበሩ 37 ሰዎች መያዝ የተቻለ ሲሆን ከነሱ ጋር ንኪኪ ነበራቸው የተባሉ ከ100 በላይ ግለሰቦች ተይዘው ለይቶ ማቆያ ውስጥ መግባታቸውንም አስረድተዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።