በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ር ዐብይ በደቡብ ክልል


ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ
ጠ/ሚ ዐብይ አህመድ

ታላቅ ሃገር ሳይፈጠር ታላቅ ህዝብ ስለማይኖር ኢትዮጵያ መገንባት ቀዳሚ ተግባር መሆን እንደሚገባ በደቡብ ክልል ካምባታ ፤ ጣምባሮና ሃላባ ዞኖች ተገኝተው ከህዝብ ጋራ የተወያዩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወቅት ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ተዋግተን፣ ተከፋፍለን አይተናል ያተረፍነው ድኅነትና ኃላቀርነት ስለሆነ አሁን ከዚያ ወጥተን ነገሮችን ሁሉ በእርጋታ ማየት የሚገባን ጊዜ ላይ እንገኛለን” ብለዋል።

ፍትሃዊ የኃብት ክፍፍልና እኩል መልማት በተመለከተ ከካምባታ ጣምባሮና ሃላባ ዞኖች ህዝብ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲስጡ “ኢትዮጵያ ውስጥ ያልተገቡ ፕሮጀክቶች ሀገሪቱን ችግር ውስጥ ከቷታል፣ መንግሥት ያሉ ችግሮችን በመቅርፍ በተቻለው አቅም የህዝብ የልማት ጥያቄ ይመልሳልም ማለታቸውን የአገሪቱ የመንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ዘግበዋል።

በክልል መደራጅትን በተመለከተም ዞንም፥ ክልልም ሀገርም መሆን ትችላላችሁ ፤ መጀመሪያ ግን ሰው ሁኑ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ መንግሥት ጥያቄውን ለመመልስ ጥናት፥ ተያያዥ ምክክርና ውይይት እያካሄደ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ጠ/ር ዐብይ በደቡብ ክልል
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:20 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG