በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለጥያቄዎ መልስ፡ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምሑራን ትንታኔ ይሰጣሉ


ለጥያቄዎ መልስ በተሰኘው የትላንቱ ዝግጅታችን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከአድማጮች ለተነሱ ጥያቄዎች ምሑራን መልስ ሰጥተውበታል። “ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች መኾኑ እየተነገረ እንዴት ረሃብ ይከሰታል?” ለሚለው ጥያቄ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ፕሮፌሰር ዶክተር መሐሪ ረዳኢ መልስ ሲሰጡ ነበር ፕሮግራማችን ያበቃው፤ ዛሬ ከቆመበት ይቀጥላሉ።

በዚህ ውይይት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ፕሮፌሰር ዶክተር መሐሪ ረዳኢ፣ አንትሮፓሎጂ ፕሮፌሰር ዶክተር ዶክተር ገብሬ ይንቲሶ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፓለቲካ ሳይንስ ፕሮፌሰር ዶክተር ካሳሁን ብርሃኑ ናቸዉ፡፡ በምግብ እጥረቱ ጉዳይ የሚጀምረው ሰፊ ዝግጅት በኢትዮጵያ በወልቃይት የተነሳውን የማንነት ጥያቄም ያካትታል፡፡

የጥያቄዎ መልስ አዘጋጅና አቅራቢ ትዝታ በላቸው ናት።

ዝግጅቱን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

ለጥያቄዎ መልስ፡ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ምሑራን ትንታኔ ይሰጣሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:25:59 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

አድማጮች የዚህ ዝግጅት ክፍል ሦስት በመጪው ሳምንት ይቀርባል።ቀጣዩ ውይይት በኦሮሚያ በተነሳዉ ተቃውሞና መንግሥት በሰጠዉ ምላሽ ላይ ከአድማጮች በተላኩልን ጥያቄዎች ላይ ያተኮሩ ይሆናሉ።

XS
SM
MD
LG