በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ኢትዮጵያዊ መሆን ኩራት ነው!” ሊቀ ስዩማን ጌታሁን አጥላው


ፋይል-ፎቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
ፋይል-ፎቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድና ቨርጅኒያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሃገርን ቅርስ ባህልና ታሪክ በማስጠበቅና በማሳወቅ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል።

በዋሽንግተን ዲሲ ሜሪላንድና ቨርጅኒያ ለሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያዊ ምዕመናንን የሚያስተናግደው የርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ባህልንና ቋንቋን በማስተማር ረገድ የተጠናከረ ስራ በመስራት ላይ ይገኛል። በአሁኑ ጊዜ 320 ለሚሆኑ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከመደበኛ ትምህርት ማስጠናት ጀምሮ የኢትዮጵያ ታሪክን፣ የአማርኛ ቋንቋን የመናገርና የማንበብ ትምህርት በመሰጠት ላይ ይገኛል።

በዚሁ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን መምህር የሆኑት ሊቀ-ስዩማን ጌታሁን አጥላው የዚህን ትምህርት ፕሮግራም ለሰባት አመታት በመምራት ላይ ይገኛሉ። በኢትዮ አሜሪካውያን ልጆች ላይ የተመለከቱትን የባህል ግጭት ከመስታወት አራጋው ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ እንዲህ ይገልፁታል። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን ድምፅ ማዳመጥ ይችላሉ።

“ኢትዮጵያዊ መሆን ኩራት ነው!” ሊቀ ስዩማን ጌታሁን አጥላው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:33 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG