በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የሳውዲ አረብያ ጉብኝት


የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ከንጉስ ሳልማን ጋር ለመነጋገርና ነገ ሀሙስ ሪያድ በሚደረገው ስድስት ሃገራትን ባቀፈው የፋርስ ባህረ-ሰላጤ ሀገሮች የትብብር ካውንስል ጉባኤ ለመገኘት ሳውዲ አረብያን እየጎበኙ ነው። ባለፈው አመት ከኢራን ጋር አለም አቀፍ የኑክሌር ስምምነት ከተደረገ ወዲህ የዩናይትድ ስቴትስና የፋርስ ባህረ-ሰላጤ ሀገሮች ግንኙነት ውጥረት ሰፍኖበታል።

ዩናይትድ ስቴትስና ሳውዲ አረብያ የሶርያው ፕረዚዳንት ባሻር ዐል-ዐሳድ ፖለቲካዊ እድልን በሚመለከትም ልዩነት አላቸው። እ.አ.አ. መስከረም 11 በ 2001 ዓ.ም. በዩናይትድ ስቴትስ በተፈጸመው የአሸባሪዎች ጥቃት ሰለባ የሆኑት ቤተሰቦች በሳውዲ አረብያ ላይ ክስ እንዲመሰረቱ የዩናይተድ ስቴትስ ህግ በመፍቀዱም ሳውዲ አረብያ ስጋት አላት።

የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጆሽ ኤርነስት ግን የዩናይትድ ስቴትስና የሳውዲ አረብያ ግንኙነት ከኢራን ጋር በተደረገው የኑክሌር ስምምነት ምክንያት ሻክሯል የሚለውን አባባል እንደማይቀበሉ ትላንት ማክሰኞ ጠቁመዋል።

“በአከባቢው ካሉት ዋና ዋና ተቀናቃኞችዋ ሀገሮች አንዷ ኑክሌ መሳርይ ልተራ የማትችልበት ሁኔታ የሚረጋገጥ መሆኑን ሲያውቁ የሳውዲ አረብያ ብሄራዊ ጸጥታ ይረጋገጣል ማለት ነው። ይህም ለሳውዲ አረብያ ጥሩ ነገር ነው። ምክንያቱም የጸጥታ ሁኔታቸውን ያጠነክራል። ዩናይትድ ስቴትስ ኢራን የኑክሌር መሳርያ ባለቤት እንዳትሆን የተደረገውን ዲፕሎማስያዊ ጥረት ባትመራ ኑሮ እንዲህ አይነት ሁኔታ ባልተፈጠረ ነበር።”ብለዋል።

ባዛም ላይ “ዋሽንግተንና የፋርስ ባህረ-ሰላጤ ሀገሮች በጽንፈኞች ላይ በሚካሄደው ውጊያ በወታደራዊ እርምጃና በረድኤት ተግባር እየተባበሩ ነው። ሰዎችን በኢንተርነት ለመመልመል የሚያደርጉትን ጥረት በመቋቋማና እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ጽንፈኛ ቡድን የገንዘባዊ ተቋማት ተደራሽነት እንዳይኖረው በማድረግ ረገድም እየተባበሩ ነው” ብለዋል የዋይት ሀውሱ ቃል አቀባይ።

ፕረዚዳንት ኦባማ እአአ በ 2009 ዓ.ም. ስልጣን ከያዙበት ጊዜ አንስቶ የፋርስ ባህረ-ሰላጤን ሲጎበኙ ለአራተኝ ጊዜ ነው። ዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው ዊልሰን ማዕከል የመካከለኛው ምስራቅ ጉዳይ ጠቢብ የሆኑት ዴቪድ ኦቶዌ የፕረዚዳንት ኦባማ ጉብኝት ዩናይተድ ስቴትስ ከሀገሮቹ ጋር ያላት ግንኑነት ዘላቂ መሆኑን ለአረብ አጋር ሀገሮች ለማረጋገጥ እንድሆነ አስገንዝበዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ ወደ ጀርመንም ጎራ ይላል። ምናልባትም የመጨረሻው ኦፊሴላዊ ጉብኝታቸው ሊሆን ይችላል። ከጀርመንዋ ቻንስለር አንጌላ መርኬል ጋር ይነጋገራሉ። ብሪታንያ በአውሮፓ ህብረት አባልነት ለመቆየት ወይም ላለመቆየት በመጪው ሰኔ ወር ህዝበ-ውሳኔ ከማካሄድዋ በፊት ብሪታንያ በአባልነት እንድትቀጥል ፕረዚዳንት ኦባማ ጥሪ እንዲያቀርቡ ይጠበቃል።

የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ዘጋቢ ቪክተር ቢቲ ያጠናቀረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ የሳውዲ አረብያ ጉብኝት
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:06 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG