በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩስያ በሳዑዲንና በኢራን መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለመሸምገል ፈቃደኛነቷን ገለጸች


በሩስያ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች መሠረት ሞስኮ፣ የሳዑዲንና የኢራንን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለውይይት ልታግብዝ አቅዳለች።

ሪያድ፣ ታዋቂውን የሺዓይት ሃይማኖታዊ መሪ ነሚር አል ነሚርን (Nimr al-Nimr)በሞት ከቀጣች ወዲህ፣ ከኢራን ጋር የተፈጠረውን ውዝግብ ለመሸምገል ሩስያ ፈቃደኛነቷን ገለጸች።

በሩስያ ዲፕሎማሲያዊ ምንጮች መሠረት ሞስኮ፣ የሳዑዲንና የኢራንን ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለውይይት ልታግብዝ አቅዳለች።

"የሁለቱ መንግሥታት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሮች ለመወያየት ፈቃደኞች ከሆኑ፣ ዕቅዳችን ሥራ ላይ ዋለ ማለት ነው" ሲሉ፣ ምንጮቹ ለሩስያው መንግታዊ ዜና አውታር ቲኤ ኤስ ኤስ (TASS) ገልጸዋል።

ይሁንና፣ የሞስኮው ካርነጊ (Carnegie) ማዕከል ኒኮላይ ኮዛኖቭ (Nikolay Kozhanov) እንደሚሉት፣ ሩስያ ከኢራን ጋር ያላት ወዳጅነት፣ ለሳዑዲ አረቢያ የሚመቻት አይሆንም።

"አንድን ውዝግብ ወይም ግጭት ለመሸምገል፣ ገለልተኛ አቋም መያዝ ያስፈልጋል" ሲሉም ያክላሉ ኮዛኖቭ።

XS
SM
MD
LG