በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ ሳዑዲ መሩን ጥምረት እንደምትደግፍ አስታወቀች


የኤርትራ ካርታ
የኤርትራ ካርታ

በሳዑዲ አረቢያ ለሚመራው ፀረ-ሽብር ጥምረት ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጅ መሆኑን የኤርት መንግሥት አስታወቀ፡፡

በሳዑዲ አረቢያ ለሚመራው ፀረ-ሽብር ጥምረት ሙሉ ድጋፍ ለመስጠት ዝግጅ መሆኑን የኤርት መንግሥት አስታወቀ፡፡

የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ባለጣው መግለጫ በሽብር ፈጠራ ለይ ለመዝመት የሚያስችል ጥምረት ለመፍጠር በሳዑዲ አረቢያ የተነሣሣው ጅማሮ በአባባቢያችንና በመላው ዓለምም ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ቁልፍ እርምጃ ነው” ብሏል፡፡

“ሃሣቡ ሽብር ፈጠራና ሕግ አልበኝነትን ለመዋጋትና በአካበቢውም ሰላምና ፀጥታን ለመረጋገጥ የሚያስችል ሰፊ ሥልት ያለው ትብብር ለመፍጠር እየተካሄደ ያለው ተግባር አካል እንደሆነ የኤርትራ መንግሥት ያምናል” ብሏል፡፡

“በዚህም መንፈስ - አለ መግለጫው በማጠቃለያው - የኤርትራ መንግሥት ጅማሮውን ያለመቆጠብ ለመደገፍና ለጥምረቱም ማበርከት የሚችለውን ለማበርከት ዝግጁ መሆኑን ይገልፃል፡፡”

XS
SM
MD
LG