በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሳዑዲ-መራሹ ጣምራ ጦር 9 የሳዑዲ እስረኞች ስለተለቀቁ፣ በቁጥጥሩ ስር የነበሩ 109 የየመን እስረኞችን እንደፈታ አስታወቀ


ሳዑዲዎቹ እንዴትና መቼ እንደታሰሩ የጣምራው መግለጫ የሰጠው ዝርዝር የለም፤ ይሁን እንጂ የመኒዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሳዑዲ ድንበር አካባቢ መሆኑን አምክቷል።

የመን ውስጥ ከሺዓይት ሙስሊሞች ጋር የሚዋጋው ሳዑዲ-መራሹ ጣምራ ጦር፣ 9 የሳዑዲ እስረኞች ስለተለቀቁ፣ በቁጥጥሩ ስር የነበሩ 109 የመኒ እስረኞችን እንደፈታ፣ ዛሬ ሰኞ አስታወቀ።

ሳዑዲዎቹ እንዴትና መቼ እንደታሰሩ የጣምራው መግለጫ የሰጠው ዝርዝር የለም፤ ይሁን እንጂ የመኒዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ሳዑዲ ድንበር አካባቢ መሆኑን አመልክቷል።

የሺዓይት ሁቲ (Houthi) ሽምቅ ተዋጊዎች የየመንን ዋና ከተማ ሳንዓን የተቆጣጠሩት እ.አ.አ. በመስከረም 2014 ዓ.ም. መሆኑ ይታወቃል።

ከዚያም፣ እ.አ.አ. ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር፣ እስከ አደን (Aden) ወደብ ድረስ ወደ ደቡብ በመግፋት፣ ለፕሬዚደንት አብዱ ራቡ ማንሱ(Abdu Rabu Mansour Hadi) ወደ ሳዑዲ አረቢያ መሰደድ ምክኒያት መሆኑም አይዘነጋም። ከዚያ ወዲያ ነው ሳዑዲ አረቢያ ጣምራ ጦር አቋቁማ በሁቲ ሸማቂዎች ላይ የአየር ጥቃት እያካሄደች ነው።

በግጭቱ፣ ከ6,000 ሕዝብ በላይ ሕይወቱን እንዳጣበትም አይዘነጋም።

XS
SM
MD
LG