በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ሳዑዲና ኢራንን ለማግባባት እየሞከረች ነው


በሳዑዲ ኤምባሲ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ኤርትራ አውግዛለች።

በሺአውን ሳዑዲ አረቢያዊ የዕምነት መሪ ሼኽ ኒምር አል-ኒምር ባለፈው ዓመት ተላልፎባቸው የነበረ የሞት ፍርድ ሰሞኑን ከተፈፀመባቸው ወዲህ በሳዑዲ አረቢያና በኢራን መካከል የተነሣውን የተጋጋለ ውጥረት ለማርገብ የታሰበ ‘ጥንቃቄ የተሞላበት’ የተባለ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ዩናይትድ ስቴትስ መጀመሯ ተወርቷል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ጃን ኬሪ የሁለቱንም ሃገሮች ባለሥልጣናት እያገኙ ንትርካቸውንና መፋጠጣቸውን እንዲያረግቡ ለማግባባት እየሞከሩ ነው፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በአካባቢው ያሉ ጥቅሞቿ በሁለቱ የክልሉ ኃያላን መጋጨት የበዛ ጉዳት ሊደርስባቸው እንደሚችል በማሰብ እየሠጋች መሆኗ እየተነገረ ነው፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የአካባቢው ሃገሮችና ታጣቂ ኃይሎች ጎራ እየለዩ ከሁለቱ ጀርባ መሰለፍ መቀጠላቸውንና የውጥረቱ ተፅዕኖ እየተንፀባረቀ መሆኑን ተንታኞች እየተናገሩ ነው፡፡

እንዲሁም ቴህራን ውስጥ በሳዑዲ ኤምባሲ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ኤርትራ አውግዛለች፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

አሜሪካ ሳዑዲና ኢራንን ለማግባት እየሞከረች ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:59 0:00

XS
SM
MD
LG