በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሳዑዲ የሚመራው ያየር ድብደባ በየመን ሲቪሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው

ፋይል ፎቶ - በሳዑዲ የሚመራው ያየር ድብደባ በየመን በቀይ ባህር አከባቢ በምትገኝ ከተማ ሑዴዳ (Houdieda) [ሮይተርስ/ REUTERS]
ፋይል ፎቶ - በሳዑዲ የሚመራው ያየር ድብደባ በየመን በቀይ ባህር አከባቢ በምትገኝ ከተማ ሑዴዳ (Houdieda) [ሮይተርስ/ REUTERS]

ሳዑዲ በየመን የሚመራው ያየር ድብደባ ከ8 ሽህ በላይ የሲቪሎች ህይወት ማጥፋቱና ማቅሰሉ እናም ቀዳሚ ጠንቅ መሆኑ ታወቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አዲስ ይፋ ያደረገው ሪፖርት፥ በየመን እየተካሄደ ያለው ግጭት በምን ያህል ሲቪሎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ያሳያል። በድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ሪፖርት መሠረት፥ ካለፈው ያውሮፓውያኑ ዓመት 2015 መጋቢት 26 እስከ ዓመቱ ማብቂያ፥ ከ 8,100 በላይ ሲቪሎች ተገድለዋል ወይም ቆስለዋል። አብዛኞቹ ሰዎች የተገደሉት ደግሞ፥ በሳዑዲ በሚመራው ህብረ ብሄር ኃይሎች ያየር ድብደባ መሆኑን ያስረዳል።

ሊሳ ሽላይን (Lisa Schlein) ከጂኒቫ ለአሜሪካ ድምፅ የላከችው አጭር ዘገባ አለ። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል ከተያያዘው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

በሳዑዲ የሚመራው ያየር ድብደባ በየመን ሲቪሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00

XS
SM
MD
LG