በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሳውዲ አረቢያ በበርካታ ሰዎች ላይ የፈጸመችው የሞት ቅጣት ዓለም አቀፍ ውግዘት አስከትሏል


ታዋቂ የሺያ ሃይማኖት መሪውን ጨምሮ አርባ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ በበርካታ ሙስሊም ሃገሮች በሳውዲ ንጉሣዊ ቤተሰብ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። የሳውዲ አረቢያ እስላማዊ ፍርድ ቤቶች ሁከት አልባ ወንጀሎች በፈጸሙ ሰዎች ላይ ጭምር የሞት ቅጣት ይፈርዳሉ፣ የፍርድ ሂደቶችም የሚከናወኑት በሚስጥርና ኢፍትሃዊ በሆነ መንገድ ነው በማለት የሰብኣዊ መብት ቡድኖች ለረጅም ጊዜ ሲያስጠነቅቁ ቆይተዋል።

ተቃዋሚ ሰልፈኞች የሞት ቅጣት ፍርድ ከተፈጸመባቸው አንዱ የሆኑትና ብጥብጥ በማነሳሳት የተበየነባቸውን የታወቁ የሳውዲው ንጉሣዊ ቤተሰብ ነቃፊ ሼክ ኒምር አል ኒምርን ፎቶግራፍ ይዘው ወጥተዋል። ታዋቂው የሃይማኖት መሪ ነጻ ምርጫ እንዲካሄድ ሲጠይቁ የነበሩ ሲሆን እአአ በ 2012 ዓ.ም. በሀገሪቱ በተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ነው የታሰሩት።

በኢራቅ ባግዳድ የከተማ ምክር ቤት አባል ፋላህ አል ጃዛኢሪ “ሼክ ኒምርን በኣሸባሪነት ለመፈረጅ ያደረጉትን ውሳኔ ማናቸውም ኢራቃዊ ማናቸውም የኢራቅ ህዝብ ሃሳብ አፍላቂ ያወገዘው ተግባር ነው” ብለዋል።

ትናንት ዕሁድ የሊባኖስ የሺያዎች ሽምቅ ተዋጊ ቡድን ሄዝቦላ መሪ ሃሳን ናስራላ በቴሌቭዢን በተላለፈ ንግግር በሳውዲ አረቢያ ላይ ውግዘት ያወረደባት ሲሆን የተሰበሰበው ህዝብ “ሞት ለሳኡድ ቤተሰብ” በማለት መፈክር አሰምቱዋል።

“የሼህ ኒምር መገደል የሳውዲ መንግሥት መልዕክቱን የሚያስተላልፈው ደም በማፍሰስ በጎራዴ እና አንገት በመቅላት መሆኑን ለአረብ እና ለሙስሊሙ ዓለም የሚያረግግት ነው። የሳዊዲ ገዢዎች ለተቀረው ሙስሊሙ ዓለም ሌሎች የሃይማኖቱ ዕምነቶች ወይም ደግሞ ደንታ እንደሌላቸው ያሳያል። ለሙስሊሞችም ሆነ ባጠቃላይ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ አስተያየት ጉዳያቸው እንዳልሆነ የሞት ቅጣቱን አትፈጽሙ ብለው ሲለምኑዋቸው የነበሩትን ወዳጆቻቸውን ጭምር ከምንም እንዳልቆጠሩ ያመለክታል”ብለዋል።

የሳውዲ አረብያ ሙስሊሞች አብዛኖቹ ሱኒዎች ሲሆኑ ህጉዋም ሸሪያ ላይ የተመሠረተ ነው። የሺያ እስልምና መሪዎች የሳውዲ መሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ በጥብቅ እንዲወገዙ እያሳሰቡ ናቸው።

ሼክ ሞሃመድ አል ባሼክ “የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና በዓለም ዙሪያ ያሉ የሰብዓዊ መብት ቡድኖች የሳኡድ ቤተሰብን ፈላጭ ቆራጭነት እጥብቀው እንዲቃወሙ በሼህ ኒምር ላይ የፈጸሙትን ወንጀል እንዲያወግዙ እንጠይቃለን። ዓለም ኣሁን ካልተናገረ መቼ ሊናገር ነው?” ብለዋል።

ሳውዲ የሚገኙት የእስልምና ሃይማኖት እጅግ ቅዱሳን ስፍራዎች መካ እና መዲና በንጉሡ ቁጥጥር ስር መሆናቸው በዓለም ዙሪያ በበርካታ ሙስሊሞች ዘንድ አይወደድም።

የአካባቢው የሺያዎች መሪ አላማ አልጃዝ ሁሴን ባሄሽቲ “ሳውዲ ኣረቢያ ቅዱሳን ቦታዎቹን ለሙስሊም ሃገሮች የጋራ ቁጥጥር እንድታስረክብ ዛሬ በኣል ኒምር ሰማዕትነት ቀን ባለ ሃይላችን ወጥተን እንጠይቃለን። ሳውዲ ቅዱሳን ስፍራዎችን ለመጠበቅ ብቁ ኣይደለችም። ሙስሊም ሃገሮች በሙሉ በጋራ ሆነው ቅዱሳን ስፍራዎቹን መቆጣጠር ኣለባቸው” ብለዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ኢራን ዋና ከተማ ውስጥ የሚገኘውን የሳውዲ ኤምባሲ ተቃዋሚዎች ወረው ጣቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ ሳውዲ ከእራን ጋር ያላትን ግንኙነት ማቁዋረጡዋን ተከትላ የሳውዲ ወዳጅ ባህሬይን ተመሳሳይ ርምጃ ወስዳለች።

ባህሬይን የኢራን ዲፕሎማቶች በኣርባ ስምንት ሰዓት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ ማዘዙዋ የተገለጸ ሲሆን ሳውዲም ትናንት በሁለት ቀን ውስጥ እንዲወጡ ኣዛለች።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ኣቀባይ ሆሴን ጃበር ኣንሳሪ የሳውዲን ውሳኔ ኣውግዘው ርምጃው በክልሉ ውጥረቱን ያባብሳል ብለዋል።

ቴህራን በሚገኘው ኢምባሲ ተቃዋሚዎች ቁሳቁስ ከመሰባበራቸው ቃጠሎ ከማስነሳታቸው ሌላ ማሻድ ከተማም የሚገኘውን ቆንስላም ወረዋል። ቢያንስ ኣርባ ተቃዋሚ ሰልፈኞች ታስረዋል። የኢራን ፕሬዚደንት ሃሳን ሩሃኒ የተቃዋሚዎቹ ተግባር “ፈጽሞ ሊሆን የማይገባው ነው” ብለዋል። ፕሬዚደንቱ የሼህ ኒምርን መገደል አውግዘዋል።

የሳውዲ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ኣደል ኣል ጁቤይር ብዙሃኑ ህዝቡዋ ሱኒዎች የሆነቸው ሀገራቸው “በሺያዎች የምትመራው ኢራን የሀገራችንንም ሆነ ባጠቃላይ የክልሉን ሰላም እንድታደፈርስ ኣትፈቅድላትም” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በበኩሉ የአካባቢው ሃገአሮች የተፈጠረውን ውጥረት የሚያረግብ ገንቢ ርምጃ እንዲወስዱ መወትወታችንን እንቀጥላለን ብሏል። በሊባኖስ ባህሬይናና ህንድ እንዲሆም ለንደን በምገኘው የሳውዲ ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጉዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን በሼህ ኒምር ኣል ኒምር ላይ የተፈጸመው የሞት ቅጣት ፍርድ ኣሳዝኖናል ድርጊቱን በተምለከት የሚሰጡት ምላሾች ርጋታና መቆጠብ ያልተለያቸው እንዲሆኑ ተማጽነዋል።

የኒምር መገደል በክልሉ ያለውን ሃይማኖታው ውጥረት ያባብሳል ስትል ዩናይትድ ስቴትስት ስጋትዋን ገልጻለች። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጃን ከርቢ ቅዳሜ ባወጡት መግለጫ የታዋቂው የሺያዎች መሪ የፖለቲካ ታጋይ መገደል ባሁኑ ጊዜ እንዲረግብ የሚፈለገውን የሃይማኖት ውጥረት ያባብሳል ብለዋል።

እአአ በ 1979 ዓ.ም. በተካሄደው የኢራን አብዮት ኣክራሪ ሺያ ሃይማኖት መሪዎች ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ወዲህ ኢራንና ሳውዲ ኣረቢያ ሙስሊሙን ዓለም መሪነት ለመቆጣጠር ሲፎካከሩበት ኖረዋል፣ የዩናዩናትድ ስቴትስ የኢራቅ ጦርነት ኣኢራቅ ውስጥ ሺያ መር መንግሥት መተከሉ ያሃይማኖታን የብሂረሰብ ውጥረቱን ኣባባሰው። በክልሉ የሃያማኖታዊ ሚዛንም ወሳኝ ለውጥ ተፈጠረ።

እ አአ ከ2011 የረቦች ኣመጽ በሁዋል ኣደግሞ ሳውዲና ኢራን በሶሪያው ጦርነት ለተቀናኝ ወገኖች ድጋፍ በመስጠት በከባድ የእጅ ኣዙር ጦርነት ተጣመዱ ። ሁለቱ ሃገሮች የመን ውስጥም ተቀናቃኝ ወታደራዊ ኣንጃዎችን የሚያግዙ ሲሆን ሳውዲ የምትመራው ህበረት ላለፉት ዘጠኝ ወራት በኢራን በሚደገፉ የሺያ ይዞታዎች ላይ ቦምብ ሲያዘንብ ቆይቱዋል።

ዘላቲካ ሆኬ (Zlatica Hoke) ያጠናቀረችውን ዘገባ ቆንጂት ታዬ አቅርባዋለች። ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

በሳውዲ ንጉሣዊ ቤተሰብ የተካሄደ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:47 0:00

XS
SM
MD
LG