በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢራንና በሳዑዲ አረቢያ መካከል የተፈጠረው ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ዛሬ ይበልጥ ተካሯል


የሱዑዲ አረቢያ ንጉስ ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ እአአ 2015[ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/ REUTERS]
የሱዑዲ አረቢያ ንጉስ ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝ እአአ 2015[ፋይል ፎቶ - ሮይተርስ/ REUTERS]

ቴህራን ከሳዑዲ ታስመጣቸው የነበሩ የንግድ ቁሳቁሶችን በሙሉ አግዳለች።

በኢራንና በሳዑዲ አረቢያ መካከል የተፈጠረው ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ዛሬ ይበልጥ ተካሯል። ቴህራን ከሳዑዲ ታስመጣቸው የነበሩ የንግድ ቁሳቁሶችን በሙሉ አግዳለች።

ሱዑዲ አረቢያ የመን በሚገኘው ኤምባሲ ላይ ያየር ጥቃት ያካሄደችው ሆን ብላ ነው ስትልም ሪያድን ከሳለች።

የመን
የመን

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሁሴን ጃብር አንሳሪ (Hossein Jaber Ansari) ሲናገሩ፥ በየመን ዋና ከተማ በሰንዓ ኢራን ኤምባሲ ላይ የተፈጸመው ያየር ጥቃት ለዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮዎች ጥበቃ እንዲደረግ የሚጠይቀውን ዓለም አቀፍ ህግጋት በሙሉ የጣሰ ነው ብለዋል።

በኤምባሲው ሕንፃና ባንዳንድ ዲፕሎማቶች ላይ ለደረሰው ጉዳት ኃላፊነቱ የሳዑዲ አረቢያ ነው ሲሉም ቃል አቀባዩ አክለዋል። መግለጫቸው ጉዳት የደረሰባቸው የኤምባሲው ሠራተኞች እነማን መሆናቸውን ግን አያብራራም።

XS
SM
MD
LG