በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአል-ሸባብ አዛዦች በአፍሪቃ ህብረትና በሶማልያ ብሄራዊ ሰራዊት እንደተገደሉ የህብረቱ መግለጫ አስታወቀ

ፋይል ፎቶ- የአፍሪቃ ህብረት ሰላም ጠባቂ ሀይሎች በሶማልያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ
ፋይል ፎቶ- የአፍሪቃ ህብረት ሰላም ጠባቂ ሀይሎች በሶማልያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ

የአከባቢው የአል-ሸባብ የስለላ ክፍል ሀላፊ ሐሰን ዐሊ ድሁሬ እንደተገደለ ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል። የአማጽያኑ ቃል አቀባይ ድሁሪም እንደተገደለ ገልጿል። ስለሌሎቹ ግን ማረጋጋጫ አልሰጠም።

ስድስት ተጨማሪ የአል-ሸባብ ወታደራዊ አዛዦች ካለፉት ጥቂት ቀናት ወዲህ በአፍሪቃ ህብረት ሰላም ጠባቂ ሀይሎችና በሶማልያ ብሄራዊ ሰራዊት እንደተገደሉ የአፍሪቃ ህብረት ተልእኮ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

የአከባቢው የአል-ሸባብ የስለላ ክፍል ሀላፊ ሐሰን ዐሊ ድሁሬ እንደተገደለ ሮይተርስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል። የአማጽያኑ ቃል አቀባይ ድሁሪም እንደተገደለ ገልጿል። ስለሌሎቹ ግን ማረጋጋጫ አልሰጠም።

የሶማልያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ካርታ
የሶማልያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ካርታ

የተባበሩት ሃይሎች በአሸባሪው ቡድን ላይ የሚያካሄዱትን ውጊያ ባጠናከሩበት በአሁኑ ወቅት በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ የተገደሉት የጽንፈኛው ቡድን ወታደራዊ አዛዦች ሰባት ደርሰዋል ማለት ነው።

የአል-ሸባብ ታጣቂ
የአል-ሸባብ ታጣቂ

ባለፈው ቅዳሜ በተባበረው ሃይል ጃንዐሌ ላይ የተገደለው የአል-ሸባብ ወታደራዊ አዛዥ አብዲራሽር ቡግዱቤ የተባለው ነው። ሌሎቹ ደግሞ የሊጎ የአል-ሸባብ አዛዥ ሼኽ መሐመድ ዓሊ፣ በጃንዐሌ የአል-ሸባብ ዳኛ የነበረው መሐመድ አብሪባኦና ዋናው አሰልጣኝ ሼኽ ማንሱር እንደሚገኙባቸው የአሚሶም መገጫ ጠቅሷል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG