በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል-ሸባብ በአፍሪቃ ህብረት ወታደራዊ ሰፈር ላይ ባደረሰው ጥቃት በርካታ የኬንያ ወታደሮች እንደተገደሉ ተገለጸ


የአል-ሸባብ ታጣቂ
የአል-ሸባብ ታጣቂ

በደቡብ ሞዕራብ ሶማላያ ጌዶ ክልል ውስጥ ኤል-አዴ በተባለው መንደር በሚገኘው የአሚሶም ማለት በሶማልያ የአፍሪቃ ህብረት ሰላም ጥበቃ ተልእኮ ሰፈር ላይ ዐል ሸባብ ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 35 ሰላም ጠባቂዎች እንደተገደሉ ተዘግቧል። ዘገባውን ያዘጋጀው በአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሶማልያ አገልግሎት ክፍል ሲሆን አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

በሶማልያ ጌዶ ክልል ያሉት ባለስልጣኖችና እማኞች የአል-ሸባብ አማጽያን ኤል-አዴ አጠገብ በሚገኘው የአፍሪቃ ህብረት ወታደራዊ ሰፈር ላይ ጥቃት እንደከፈቱ ገልጸዋል።

አጥቂዎቹ ቢያንስ አራት በፈንጂዎች የተሞሉ መኪኖችን ከሰፈሩ ዋና በር ጋር እንዳጋጩና ከፍንዳታው ባኋላ በአማጽያኑና በኬንያ ወታደሮች መካከል ከባድ የተኩስ ልውውጥ እንዳተካሄደ ተዘገቧል።

የጌዶ ክልል ምክትል አስተዳዳሪ መሐመድ ሑሰን አይሳክ አብራርተዋታል።

“አል-ሸባብ በኬንያ ወታደሮች ላይ ጥቃት ከከፈተ በኋላ ከባድ ውጊያ ተካሄደ። ከ 35 እስከ 40 የሚሆኑ የኬንያ ወታደሮች ተገድለዋል። በርካታ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎች ጋይተዋል። በሚገባ የታቀደና ከባድ ጥቃት ነው የተፈጸመው። እጥቂዎቹ አራት በፈንጂዎች የተሞሉ መኪኖችን ከወታደራዊው ሰፈር ዋና በር ጋር አጋጭተው አፈንዱ።”

የኬንያው ፕረዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በበኩላቸው ሀገራቸው በአል-ሸባብ ጥቃት “አትንበረከክም” ብለዋል። ኬንያ በጥቃቱ የተሳተፉትን ወንጀለኞች አሳዳ ታገኛቸዋለች። የወታደሮቻችን ደም በከንቱ አይፈስም ሲሉም አስገንዝበዋል።

አል-ሸባብ ከ 60 በላይ የሚሆኑ የኬንያ ወታደሮችን ገድያለሁ ይላል። ምክትል የጌዶ አስድተዳዳሪ በበኩላቸው ከ 35 እስከ 40 ወታደሮች ተገድለዋል ብለዋል። አንዳንድ የኬንያ ወታደሮች ለማምለጥ እንደቻሉም አውስተዋል።

ሶማልያ ጌዶ ክልል ካርታ
ሶማልያ ጌዶ ክልል ካርታ

የኬንያ ተዋጊ ጄቶች ዐል-ዐዴ አከባቢ ያሉትን የዐል ሸባብ አማጿንን እንደደበደቡና ቢያንስ ሁለት ትጥቅ የያዙ የአማጽያን መኪኖችን እንደደመሰሱ የጌዶው ምክትል አስተዳዳሪ ጠቁመዋል።

በሶማልያ የአፍሪቅ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ልዩ ተወካይ አምባሳደር ፍራንሲስኮ ማዴራ በወታደራዊ ሰፈራቸው ላይ የተፈጸመውን ጥቃት በጥብቅ አውግዘዋል።

የሶማልያ መከላከይ ሚኒስትር አብዲቓድር ሼኽ ዐሊ ዲኒ ባወጡት መግለጫ በአፍሪቃ ህብረት ሰፈር ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አውግዘዋል።

“የአሸባሪ ቡድኖች ጥቃት” የሶማልያ ወታደራዊ ሀይልንና የአፍሪቃ ህብረት ወታደሮችን ጠላቱን ከማጥፋት ጥረታቸው አይገታም ብለዋል። ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

አል-ሸባብ በአፍሪቃ ህብረት ወታደራዊ ሰፈር ላይ ባደረሰው ጥቃት በርካታ የኬንያ ወታደሮች እንደተገደሉ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:28 0:00

XS
SM
MD
LG