በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያ የምርጫ ሂደት አንድ ሰው አንድ ድምፅ በሚለው አሰራር ለመጠቀም ተስማምተዋል


ፋይል ፎቶ - የሶማልያ ህግ አርቃቂዎች በፓርላማ ጽ/ቤት ሞቃድሹ እ.አ.እ. 2014
ፋይል ፎቶ - የሶማልያ ህግ አርቃቂዎች በፓርላማ ጽ/ቤት ሞቃድሹ እ.አ.እ. 2014

የሶማልያ ማዕከላዊ መንግሥት፣ ጎሣን መሠረት አድርጎ መሪዎችን የመምረጡን አሠራር አስወግዶ አንድ ሰው አንድ ድምፅ በሚለው ሂደት ለመተካት ተስማምተዋል።

የሶማልያ ማዕከላዊ መንግሥት እና በከፊል ነፃ የሆነችው የፑንትላንድ ግዛት ባለሥልጣናት፥ ከዘንድሮው ምርጫ በኋላ፥ ጎሣን መሠረት አድርጎ መሪዎችን የመምረጡን አሠራር አስወግደው፥ አንድ ሰው አንድ ድምፅ በሚለው ሂደት ለመተካት ተስማምተዋል።

እርምጃው በሶማልያ ለዓመታት የቆየውን የፖለቲካ አለመረጋጋትና ግጭቶች ሊያስወግድ የሚያስችል አንድ እጅግ ጠቃሚ እርምጃ ሊሆን ይችላል ተብሎ ይገመታል።

ሞሐመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያደረሰን አጭር ዘገባ አለ። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የሶማልያ የምርጫ ሂደት አንድ ሰው አንድ ድምፅ በሚለው አሰራር ለመጠቀም ተስማምተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:35 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG