በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማልያ የኢራን ዲፕሎማቶች በ72 ሰዓታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ የጊዜ ገደብ መስጠቷ ታውቋል


ሶማልያ ካርታ
ሶማልያ ካርታ

ሶማልያ ከኢራን ጋራ የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች፣ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡም የ72 ሰዓታት የጊዜ ገደብ መስጠቷ ታውቋል።

ሶማልያ ከኢራን ጋራ የነበራትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች፣ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡም የ72 ሰዓታት የጊዜ ገደብ መስጠቷ ታውቋል።

የሶማልያ ውጩ ጉዳይ ሚንስትር ዶ/ር አብዱሰላም ሃድየ ኦማር (Dr. Abdisalam Omar Hadliye) ለአሜሪካ ድምፅ የሶማልኛ አገልግሎት በሰጡት ቃል፣ የኢራን ዲፕሎማቶች ከዲፕሎማሲያዊ ተልዕኳቸው ውጪ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በመገኘታቸው ድርጊቱን አውግዘው፣ እርሳቸውም ሆኑ መንግሥታቸው ይህንኑ ተገቢ ያልሆነ እንቅስቃሴ ለኢራን መንግሥት ቢያሳውቁም፣ ምንም አጥጋቢና እርምት የተወሰደበት መልስ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል።

ዶ/ር አብዱሰላም ሃድየ ኦማር (Dr. Abdisalam Omar Hadliye)
ዶ/ር አብዱሰላም ሃድየ ኦማር (Dr. Abdisalam Omar Hadliye)

ይህ የሶማልያ እርምጃ፣ በሳዑዲ አረቢያና በሱኒው የኢራን መንግሥት መካከል ካለው ግጭት ጋር የተገናኘ እንደሆን የተጠየቁት ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ፣ ሶማልያ የመን ውስጥ ውጊያ ላይ ያለው የሳኡዲው ጣምራ ጦር አባል እንደመሆኗ «አዎ ግንኙነት ሊኖረው ይችላል» ብለዋል።

የሶማልያው ባለሥልጣን አክለውም፣ በአንድ ሬስቶራንት ውስጥ የተገኙ ሁለት የኢራን ዜጎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG