በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማልያዋ አፍጎዬ ከተማ በደረሰ የአል-ቃዒዳ ጥቃት ቢያንስ 11 ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸው ታወቀ

አፍጎዬ እና ሞቃዲሹ፣ የሶማልያ ካርታ
አፍጎዬ እና ሞቃዲሹ፣ የሶማልያ ካርታ

ከሞቅዲሾ በምዕራብ በኩል 30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ያለችው የአፍጎዬ ወረዳ ኰሚሽነር አብዱላሂ ሃሰን እንደተናገሩት፣ ነውጠኞቹ ተከታታይ ስድስት ዙር ጥቃት አካሂደው በተለያዩ ስፍራዎች የነበሩ ሲቪሎችን ገድለዋል።

ትናንት ማታ በሶማልያዋ በአፍጎዬ Afgoye ከተማ በደረሰ የአል-ቃዒዳ ጥቃት ቢያንስ 11 ሰላማዊ ሰዎች መሞታቸውን፣ ባለሥልጣናትና የዐይን ምስክሮች አስታወቁ።

ከሞቅዲሾ በምዕራብ በኩል 30 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ያለችው የአፍጎዬ ወረዳ ኰሚሽነር አብዱላሂ ሃሰን እንደተናገሩት፣ ነውጠኞቹ ተከታታይ ስድስት ዙር ጥቃት አካሂደው በተለያዩ ስፍራዎች የነበሩ ሲቪሎችን ገድለዋል።

አማጽያኑ፣ በዚች ስትራተጂካዊት በሆነችዋ ከተማ በሚገኙ የመንግሥት ጦር ሰፈሮች ላይ ከዚህ ቀደም ባደረሱት ተመሳሳይ ጥቃት፣ 5 ሰዎች ገድለው 2 የጦር ተሸከርካሪዎችን መማረካቸው አይዘነጋም።

XS
SM
MD
LG