ዋሽንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ የጦር አውሮፕላኖች ባለፈው ቅዳሜ በሶማሊያ ባካሄዱት የዓየር ድብደባ ከ150 በላይ የአልሻባብሚሊሻዎች መገደላቸውን የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚንስቴር አስታወቀ።
የዓየር ድብደባው በአልሻባብ ላይ የተገኘ ሁነኛ ድል መሆኑን የሚናገሩ የሶማሊያ ጉዳይ አዋቂዎች ግን “አልሻባብን በመፋለምላይ ያለው የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ሠራዊት ገና ረዥም ውጊያ ይጠብቀዋል፤” እያሉ ነው።
የተገደሉት ተዋጊዎች ቁጥር ግን ተጋኗል። አልሻባብ ከአንድ መቶ በላይ ተዋጊዎቹን አንድ ቦታ አያደርግም።የዓየር ድብደባውን ያረጋገጠው የአልሻባብ ቃል አቀባይ አቡ ሙሳብ።
የሶማሊያው ፕሬዝዳንታዊ ቃል አቀባይ ዳውድ አወይስ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፤ መንግስታቸው ስለዩናይትድ ስቴትሱ የዓየር ድብደባና ውጤቱ የሚያውቅ መሆኑን፤ የደህንነት መረጃ በመስጠት መሳተፋቸውን ገልጠውየተገኘውን ድል አወድሰዋል።