ዋሽንግተን ዲሲ —
የአፍሪካ ህብረት በታወከችው ሃገራቸው ውስጥ የሚመድበው ማንኛውም የሰላም አስከባሪ ኃይል እንደ ጥቃት ስለሚቆጠር፥ ምላሽ ይሰጣል ሲሉ የቡሩንዲው ፕሬዝደንት አስጠነቀቁ።
ይህ በፕሬዘዳንቱ የተሰጠ መግለጫ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ውስጥ ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፥ ብዙዎች ደግሞ የአፍሪካ ህብረት ቀጣይ እርምጃ ምን ሊሆን ይችላል ሲሉ እንዲጠይቁ አድርጓል።
የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ አኒታ ፓወል (Anita Powell) ከጆሐንስበርግ ያደረሰችን ዘገባ አለ። ሰሎሞን ክፍሌ አቅርቦታል ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።