በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድርድር ለብሩንዲ የፖለቲካ ቀውስና እልባት


“ዋና ጸሃፊው ምክክሩ ፈር ይይዝ ዘንድ በማለም ነው ወዲህ የመጡት ብዬ አምናለሁ። በእኛም በኩል ዛሬ የምንለውና ነገም ደግመን በተመሳሳይ ልንገልጽ የምንሻው፤ ድርድር ሁሉን አቀፍ ይሁን የሚለውን ነው።” የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር Nyamitwe “ፕሬዝዳንት Nkurunziza ከተቃዋሚው ጋር መደራደር አይፈልጉም። ምክኒያቱም ብሩንዲ ዛሬ ለምትገኝበት ቀውስ ምክኒያቱ እርሳቸው መሆናቸውን ያውቃሉና” Jean Minai የብሩንዲ የዲሞክራሲ ግንባር መሪ።

የተባበሩት መንግስትታ ድርጅት ዋና ጸሃፊ ባን ኪሙን በተገኙበት አዎንታዊና ገምቢ ውይይት መደረጊን ብሩንዲ አስታወቀች። Mr Ban ትላንት ቡጁምቡራ ሲገቡ ብሩንዲ ካለችበት ቀውስ ለማዳን የአገሪቱ ፕሬዝዳንት Pirrie Nkurunziza’ን እና ሌሎች የሚመለከታቸውን አግኝተው ማነጋገራቸው ተዘግቧል።

ለወራት ለዘለቀው የብሩንዲ የፖለቲካ ቀውስ ሁነኛ እልባት ድርድር እንዲቀጥል የምትሻ መሆኑን የብሩንዲ መንግስት ለመንግስቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ ይፋ ማድረጉን የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር Nyamitwe ይፋ አድርገዋል።

ይሁንና እንዲህ ያለው ድርድር ለፍሬ ይበቃ፥ ሁሉን አቀፍ ይሆን ዘንድ የተቻለውን ያህል የብሩንዲያውያንን ሁሉ ቀልብ መግዛት አለበት፤ ባይ ናቸው።

በስደት የሚገኙት የተቃዋሚው ”የብሩንዲ የዲሞክራሲ ግንባር“ መሪ Jean Minai በበኩላቸው በቅርቡ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል፤ Pirrie Nkurunziza ከተቃዋሚው ጋር መደራደር አይፈልጉም። ምክኒያቱም ብሩንዲ ዛሬ ለምትገኝበት ቀውስ ምክኒያቱ እርሳቸው መሆናቸውን ያውቃሉና፤ ነበር ያሉት።

በሌላ በኩል፤ በያዝነው ሳምንት መገባደጂያ ወደዚያ የሚያመሩትን የአፍሪቃ መሪዎች ልዑካን ቡድን ጉዞ ተንተርሶ የብሩንዲው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር Nyamitwe በሰጡት አስተያየት መንግስታቸው የልዑካኑን ጉብኝት በአዎንታ የሚቀበል መሆኑንና በብሩንዲ ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ለመወያየት መሰናዳታቸውን ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG