በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእስራኤልና ሃማስ ግጭት የሲቪሎች ሕይወት እንዲጠበቅ አምነስቲ ጠየቀ


የእስራኤልን ተከታታይ የአየር ድብደባ ተከትሎ፣ በጋዛ፣ በጢስ ታፍናለች፡፡
የእስራኤልን ተከታታይ የአየር ድብደባ ተከትሎ፣ በጋዛ፣ በጢስ ታፍናለች፡፡

የእስራኤል የጸጥታ ኃይሎች እና የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖች የሲቪሎችን ሕይወት ለመጠበቅ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠይቋል።

“በእስራኤል፣ በጋዛ እና በእስራኤል በተያዘው ዌስት ባንክ እየጨመረ ያለው የሟቾች ቁጥር አሳስቦናል” ያለው የሰብዓዊ መብት ድርጅቱ፣ ሁሉም ወገኖች ለዓለም አቀፍ ሕግ ተገዢ እንዲሆኑ እና የሲቪል ሰዎች ደም እንዳይፈስ የሚችሉትን ሁሉ እንዲያደርጉ ጠይቋል።

“ሲቪሎችን ሆን ብሎ ኢላማ ማድረግ፣ ተመጣጣኝ ያልሆነ ጥቃት መፈጸም፣ ሲቪሎችን የሚጎዳ ወይም ሕይወት የሚቀጥፍ ጥቃት ማድረስ የጦር ወንጀል ነው” ያሉት የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ዋና ጸሃፊ አንገስ ካላማር “እስራኤል ከዚህ በፊት በጋዛ በተደረጉ ጦርነቶች የጦር ወንጀል የመፈጸም ታሪክ አላት፣ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድኖችም፣ ሲቪሎችን ኢላማ ከማድረግ እንዲቆጠቡ፣ ከዚህ በፊትም ሆነ አሁን እንደሚያደርጉት፣ በጅምላ የሚገድሉ መሣሪያዎችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ፣ ይህም እንደ ጦር ወንጀል ይቆጠራል” ሲሉ አክለዋል።

የሁከቱ መነሻ ምንጭ መፍትሄ እንዲሰጠውም አምነስቲ በሳምንቱ መጨረሻ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG