በሳምንቱ መጨረሻ፣ ሐማስ በእስራኤል ላይ በሰነዘረው ድንገተኛ ጥቃት፣ ቢያንስ ዘጠኝ አሜሪካውያን እንደተገደሉ፣ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አስታውቋል።
ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ አሜሪካውያንም ያሉበት እንደማይታወቅ፣ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማቲው ሚለርን ጠቅሶ አሶሺዬትድ ፕረስ ዘግቧል።
ያሉበት አይታወቅም የተባሉት አሜሪካውያን፥ ተጠልፈው ይወሰዱ፤ ይሙቱ ወይም ተደብቀው እንደኹ ለማወቅ አልተቻለም፤ ተብሏል።
መሥሪያ ቤቱ ከቤተሰቦቻቸው ጋራ በቅርብ እየተገናኘ እንደኾነ፣ ቃል አቀባዩ አክለው ገልጸዋል።
በሐማስ ጥቃት፣ ቢያንስ 700 የሚደርሱ ሲቪሎች እና የእስራኤል ወታደርች ሲገድሉ፣ እስራኤል በአጸፋው ባደረሰችው ጥቃት፣ በጋዛ፣ ከ400 በላይ ነዋሪዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
መድረክ / ፎረም