በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በእስራኤል ላይ የደረሰውን ህይወት የቀጠፈ የሽብር ጥቃት አወገዙ


ባይደን በእስራኤል ላይ የደረሰውን ህይወት የቀጠፈ የሽብር ጥቃት አወገዙ
ባይደን በእስራኤል ላይ የደረሰውን ህይወት የቀጠፈ የሽብር ጥቃት አወገዙ

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመቶዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያንን የገደለውን ሀማስ መር ያልተጠበቀ ጥቃት አውግዘዋል ። ክስተቱ ተቀባይነት የሌለው እና ልብ የሚሰብር መሆኑን የተናገሩት ባይደን ፣ ዋሽንግተን ለእስራኤል ጠንካራ ድጋፍ እንደምታደርግ ዳግም አስታውቀዋል።


ባይደን ይሄን መልዕክት ለማስተላለፍ በዓለም ዙሪያ እንዳሉት እንደ ብዙዎቹ እስራኤላውያን እና አይሁዶች ሁሉ ለአንድ ሳምንት የሚረዝመውን የ"ሱኩት" ኃይማኖታዊ በዓል አከባባር እያገባደዱ ከነበሩት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጋር መነጋገራቸውን አስታውቀዋል። ከዮርዳኖስ ንጉስ እና ከአሜሪካ ከፍተኛ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር መነጋገራቸውም ተገልጿል ።

አንድ ስማቸው ያልተገለጸ የባይደን አስተዳደር ከፍተኛ ባለስልጣን ዋይት ኃውስ ቀኑን ሙሉ የፍልስጤም ባለስልጣናትን፣ ቱርክ ፣ ግብጽ ፣ ሳውዳረቢያ ፣ ጀርመን ፣ እንግሊዝ እና ጣልያንን ጨምሮ ከከፍተኛ ባለስልጣናት እና መሪዎች ጋር ሲነጋገር መዋሉን በስልክ ለዘጋቢዎች አስታውቀዋል ።

የታጣቂው የፍልስጤም ቡድን የቅዳሜ ጥቃት በጥልቅ የፖለቲካ ክፍል ውስጥ በሰነበቱት የዩናይትድ ስቴትስ የሁለት ወገን ከፍተኛ የአሜሪካ ፖለቲከኞች መካከል ያልተለመደ ስምምነት ፈጥሯል። ብዙዎቹ የአመጹን ዓለም አቀፋዊ ተጽእኖ አመላክተዋል።

" ካለ አንዳች የቀደመ ትንኮሳ የተፈጸመው የዛሬው የሽብር ጥቃት እና የንጹሃን እስራኤል ዜጎች ግድያ የሃማስ እና የኢራን ድጋፍ ያላቸው አክራሪዎችን ጭካኔ አስታዋሽ ነው " ያሉት
ቀጣዩ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ለመሆን ዘመቻ እያካሄዱ ያሉት የኦሃዮ ሪፐብሊካን ተወካይ ጂም ጆርዳን ፣ "ያለ ልዩነት በወንዶች፣ በሴቶች እና በህጻናት ላይ የደረሰው ግድያ የሚያሳምም ነው።" ሲሉ አክለዋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG