በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪቃ ቀንድ ፍልሰተኞች ቁጥር በጥቂት ወራት ዉስጥ ሊጨምር እንደሚችል አይኦኤም ገለጸ


በሌዝቦስ ተቃዋሚዎች የአውሮፓ ህብረትንና የቱርክን ስምምነት እየነቀፉ እ.አ.አ 2016
በሌዝቦስ ተቃዋሚዎች የአውሮፓ ህብረትንና የቱርክን ስምምነት እየነቀፉ እ.አ.አ 2016

"ከአፍሪቃ ቀንድ አገሮች ከኤርትራ ከሱዳን ከኢትዮጵያ ሶማሊያ ፍልሰተኞች መንቀሳቀስ የሚጀምሩት በአሁኑ ጊዜ ሳይሆን ዘግዬት ብሎ በመጪዉ ወራት መሆኑን ካሁን በፊት ከነበሩት ሁኔታዎች እንረዳለን። የሚያቀኑትም ወደ ሊቢያ ነዉ፥ ከዚያም ወደ ኢጣሊያ። አሁን የሚፈልሱ ካሉም ቁጥራቸዉ ትንሽ ነዉ የሚሆነዉ በጥቂት ወራት ዉስጥ ግን ቁጥራቸዉ ይጨምራል።" የአይኦኤም ቃል አቀባይ ጆል ሚልማን (Joel Millman)

ግሪክ ባለፈዉ ወር ከአዉሮፓ ሕብረት ጋር ባደረገችዉ ስምምነት መስረት ሕግ ወጥ ፍልሰተኞችን ወደ ቱርክ መመለስ ጀምራለች። የሆነ ሆኖ ዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት አይኦኤም (IOM) ሌሎች ፍልሰተኞችና ስደተኞች ከሊቢያ ጠረፍ የሜድቴራኒያን ባህር እያቋረጡ ጣሊያን እየገቡ ነዉ መሆኑን ይናገራል።

ባለፈዉ ሳምንት ለምሳሌ ወደ አንድ ሺህ የሚሆኑ አብዛኞቹ ናይጄሪያዉያን የሆኑ ምእራብ አፍሪቃዉያን የጣሊያን ወደብ ላይ ደርሰዋል። የቀደሙ የአፍሪቃ ፍልሰተኞችን ሁኔታ በማጤን ሊከተሉ ስለሚችሉ የፍልሰት አዝማሚያዎች የተናገሩት የአይኦኤም ቃል አቀባይ ጆል ሚልማን (Joel Millman) ከሰሃራ በረሃ በታች ከሚገኙ አገሮች የሚፈልሱ ሰዎች ቁጥር በአሁኑ ጊዜ ከፍተኛ ባይሆንም የተለመደዉ የጉዞ መስመራቸዉ ሊቢያ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም ከአፍሪቃ ቀንድ አገሮች የሚፈልሰዉ ወይም የሚሰደደዉ ህዝብ ቁጥር በአገሮቹ ዉስጥ ባሉ ተጨባጭ ክስተቶች ላይ ይመረኮዛል በለዋል። "ከአፍሪቃ ቀንድ አገሮች ከኤርትራ ከሱዳን ከኢትዮጵያ ሶማሊያ ፍልሰተኞች መንቀሳቀስ የሚጀምሩት በአሁኑ ጊዜ ሳይሆን ዘግዬት ብሎ በመጪዉ ወራት መሆኑን ካሁን በፊት ከነበሩት ሁኔታዎች እንረዳለን። የሚያቀኑትም ወደ ሊቢያ ነዉ፥ ከዚያም ወደ ኢጣሊያ። አሁን የሚፈልሱ ካሉም ቁጥራቸዉ ትንሽ ነዉ የሚሆነዉ በጥቂት ወራት ዉስጥ ግን ቁጥራቸዉ ይጨምራል። ዋናዉ የስደቱ ምክንያት ደግሞ በአገሮቹ ዉስጥ ያለዉ ተጨባጭ ሁኔታ ነዉ። በኤርትራ ያለዉ የግዳጅ ዉትድርና እንዲሁም አሁን በኢትዮጵያ ያለዉ የድርቅ ሁኔታ ይባባስ እንደሆነ እነዚህ ሁሉ መሰረታዊ ምክንያቶች ናቸዉ።" ብለዋል።

ባለፈዉ ዓመት በበጋዉ ወቅት በዚህ ጊዜ የፍስተኞቹ ቁጥር እጅግ ብዙ እንደነበርና በሊቢያ በኩል አድርገዉ ዋና መዳረሻቸዉም ጣሊያን መሆኑን ተነግረዋል አይኦኤም (IOM) ቃል አቀባይ። የጣሊያን ብዙ የየስደተኞች መቀበያ በር ቢኖራትም አብዛኞቹ በሲሲሊ እንደሚገቡ የመጀመሪያዉ እርምጃቸዉ ቀድመዉ ከደረሱ ቤተሰቦች ወይም የአገራቸዉ ሰዎች ጋር መገናኘት እንደሆነ፣ አንዳንዶቹ እዚያዉ ኢጣሊያ ዉስጥ ጥገኝነት እንደሚጠይቁ የተቀሩት ደግሞ አገሪቱን ወደሚያዋስኑ በርካታ የአዉሮፓ አገሮች እንደሚዘልቁ ተናግረዋል።

አሁን ቦኮ ሃራም በምእራብ አፍሪቃ በሚያካሄደዉ ሽብር የተነሳ ከአጠቃላይ አፍሪቃ አገሮች የናይጄሪያ ፍልሰተኞ ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የዓለም አቀፉ ፍልሰት ድርጅት አይኦኤም (IOM) ቃል አቀባይ ጆል ሚልማን ተናግረዋል።

ኪም ልዊስ ያጠናቀረችውን ዘገባ፣ ትዝታ በላቸው አቅርባዋለች ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

የአፍሪቃ ቀንድ ፍልሰተኞች ቁጥር በጥቂት ወራት ዉስጥ ሊጨምር እንደሚችል አይኦኤም ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:03 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG