በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለፓሪስ ጥቃት ስደተኞች ተጠያቂ አይደሉም


ባለፈዉ አርብ አሸባሪዎች በፓሪሰ ላይ ላደረሱት ጥቃት ስደተኞችና ፍልሰተኞችን መኮነን በአዉሮፓ ጥገኝነት የማግኘት እድላቸዉን ያደናቅፋል ተባለ።

የሰብአዊ መብት ተሙዋጋች ድርጅት (Human Rights Watach) ዋና ሥራ አስኪያጅ፥ ብሩኖ ስታግኖ (Bruno Stagno) አንዳንድ ሰዎች የስደተኞች በብዛት ወደ አዉሮፓ መጉረፍ አጉሪቱንና ፈረንሳይን ለአደጋ ጋርጧል የሚሉት እዉነትነት የሌለዉ ግምት ነዉ ይላሉ።

”እኛ እስካሁን ያገኘነዉ መረጃ ያለፈዉን አርብ የፓሪስ ጥቃት ያቀዱና የፈጸሙ እዚያዉ አዉሮፓ ዉስጥ ተወልደዉ ያደጉ የፈረንሳይና የቤልጅግ ዜግነት ያላቸዉ ናቸዉ፣ ስለዚህ የስደተኞች ያደረሱት ጥቃት ነዉ የሚለዉ አነጋገር በመሰረቱ ስህተት ነዉ።”

ብሩኖ ስታግኖ (Bruno Stagno)ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የእንግሊዘኛዉ ክፍል ባልደረባችን Joe De Capua ጋር ከፓሪስ በስልክ ያደረጉትን ቃለ ምልልስ፣ ትዝታ በላቸዉ አጠናቅራለች፣ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

ለፓሪስ ጥቃት ስደተኞች ተጠያቂ አይደለም
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:49 0:00

XS
SM
MD
LG