በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ለፍልሰተኞች የተመደበውን የእርዳታ ገንዘብ ለመቋደስ የመጀመሪያዎቹ ናቸው


ፍልሰተኞች እና ስደተኞች በኢታሊ ፋይል ፎቶ [አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo]
ፍልሰተኞች እና ስደተኞች በኢታሊ ፋይል ፎቶ [አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo]

የአውሮፓ ኅብረት የመደበውን የእርዳታ ገንዘብ ባለፈው ዓመት በብዙ ሺህ የተቆጠሩ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፓ እንዲጎርፉ ያደረገውን ሥርወ-ምክንያት ለመዋጋት ነው።

በርካታ የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች የአውሮፓ ኅብረት የመደበውን የእርዳታ ገንዘብ ለመቋደስ የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ። ሁለት ቢሊዮን ዶላሩ ያስቸኳይ ጊዜ ዕርዳታ የሚውለው ባለፈው ዓመት በብዙ ሺህ የተቆጠሩ ፍልሰተኞች ወደ አውሮፓ እንዲጎርፉ ያደረገውን ሥርወ-ምክንያት ለመዋጋት ነው ተብሏል።

የአውሮፓ ኅብረት ዕቅድ በየሃገሩ የተሻለ የድንበር ጥበቃ መመሥረት፣ ምጣኔ ሃብትን ማሻሻል፣ ተፈናቃዮችና ስደተኞችን እንደ ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያና ዩጋንዳ ባሉ ሃገሮች ማስፈር ነው።

የቪኦኤው ዴቪድ አርኖልድ ሰፋ ያለ ዘገባ ያጠናቀረውን ሰሎሞን ክፍሌ አዘጋጅቶታል። ዝግጀቱን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

የአፍሪካ ቀንድ ሀገሮች ለፍልሰተኞች የተመደበውን የእርዳታ ገንዘብ ለመቋደስ የመጀመሪያዎቹ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:34 0:00

XS
SM
MD
LG