በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ አውሮፓ የሚደረግ ፍልሰትና በሴቶች ላይ የሚፈጸሙት እጅግ የከፉ የጾታ ጥቃቶች


ፋይል ፎቶ - ከሊቢያ በሜዲተራንያን ባህር በኩል አልፈው ወደ አውርሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በቤልጅግ የጦር ባህር መርከብ ነፍስ አድን ዘመቻ የዳኑ አንድ ፍልሰተኛ ኢታልያ ከገቡ በኋላ መርከቡ ውስጥ መሬት ላይ ባረፉበት ወቅት የተነሳ ፎቶ(አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)
ፋይል ፎቶ - ከሊቢያ በሜዲተራንያን ባህር በኩል አልፈው ወደ አውርሮፓ ለመሻገር ሲሞክሩ በቤልጅግ የጦር ባህር መርከብ ነፍስ አድን ዘመቻ የዳኑ አንድ ፍልሰተኛ ኢታልያ ከገቡ በኋላ መርከቡ ውስጥ መሬት ላይ ባረፉበት ወቅት የተነሳ ፎቶ(አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)

“መጠለያና ከለላ ፍለጋ ወደ አውሮፓ ከሚፈልሰው ሕዝብ መሃል የሆኑት ሴቶችና ሕጻናት ለከፉ የጾታ ጥቃቶች ይጋለጣሉ” በቅርቡ ይፋ የሆነ የተባበሩት መንግስታት አዲስ የጥናት ዘገባ።

አውሮፓ ለመግባት ረዥሙንና አደገኛውን ጉዞ የሚያያዙት ሴቶችና ሕጻናት መንገዳቸውን ሙሉ ለከፉ የጾታ ጥቃቶች እየተጋለጡ ነው፤ ሲል የተባበሩት መንግስታት አስጠነቀቀ።

ዊልያም ስፒንድለር የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት፤ ቃል አቀባይ ናቸው። በጉዳዩ ላይ፣ “አንዳንዴ ሴቶች የፍልሰት ጉዟቸውን ዳር ለማድረስ ከእነኚህ ሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ጋር ወሲብ እንዲፈጽሙ ይገደዳሉ" ብለዋል። ሴቶችንና ሕጻናትን ለጥቃት የሚያጋልጣቸው ሁኔታ "የነበራቸውን ገንዘብ ያጡና የሚጠየቁትን ከበድ ያለ ክፍያ ለማሟላት ራሳቸውን እስከ መሸጥ የሚገደዱባቸው ሁኔታዎች ተመዝግበዋል" በማለት ሃሣባቸውን ገልጸዋል።

አንዳንዴ ሴቶች የፍልሰት ጉዟቸውን ዳር ለማድረስ ከእነኚህ ሕገ ወጥ አስተላላፊዎች ጋር ወሲብ እንዲፈጽሙ ይገደዳሉ።
ዊልያም ስፒንድለር(William Spindler) የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት፤ ቃል አቀባይ

በመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት፤ የተባበሩት መንግስታት የሕዝብ ጉዳይ ተቋም እና የስደተኛ ሴቶች ጉዳይ ጽ/ቤቶች የተዋቀረ አጣሪ ልዑክ ይፋ ባደረገው የጥናት ውጤት፤ ለሴቶችና ለሕጻናት ደህንነት ጥበቃ ለማድረግ የተወሰዱት እርምጃዎች ፈጽሞ በቂ አይደሉም፤ ብሏል።

አሉላ ከበደ ያጠናቀረውን ዘገባ ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል በመጫን ያዳምጡ።

ወደ አውሮፓ ለመፍለስ መንገድ ሲገቡ ለከፉ የወሲብ ጥቃቶች ይጋለጣሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:01 0:00

XS
SM
MD
LG