በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታላቁ የኅዳሴ ግድብ Great Reninssance

ኪንሻሳ ላይ የከሸፈው የኅዳሴ ድርድር

የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር በሆኑት የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ-አንቷን ሺሴኬዲ አደራዳሪነት ዋና ከተማዪቱ ኪንሻሳ ላይ ከትናንት በስተያ ተጀምሮ የነበረው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ ድርድር ያለስኬት ተበትኗል።

ድርድሩ ሲቋረጥ በሁሉም ተደራዳሪዎች ዘንድ የንዴትና የብስጭት ስሜት ይታይ እንደነበር ኪንሻሳ የምትገኘው ሪፖርተራችን አናስታሲ ቱዴሺ ትዝብቷን ዘግባለች።

በሦስቱም ወገኖች የተንፀባረቀው የመወነጃጀል ስሜት መሆኑንም የሰጧቸው መግለጫዎች ያሳያሉ።

በአባይ ውኃ ምክንያት በአካባቢው የግጭት ሥጋት ያየለ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ግን ወገኖቹ ልዩነቶችን በማቻቻልና በመተባበር መንፈስ መነጋገራቸውን እንዲቀጥሉ አሳስቧል።

የድርድሩ ሁኔታ ኪንሻሳ ላይ ምን ይመስል እንደነበረና የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ የሆኑት የውኃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጡት መግለጫ ላይ የተጠናቀሩትን ዘገባዎች ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኪንሻሳ ላይ የከሸፈው የኅዳሴ ድርድር
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:31 0:00


የኪንሻሳ የኅዳሴ ግድብ ድርድር ያለስኬት ተበተነ

የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር በሆኑት የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ-አንቷን ሺሴኬዲ አደራዳሪነት ዋና ከተማዪቱ ኪንሻሳ የተደረገ ውይይት

የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር በሆኑት የኮንጎ ዴሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፌሊክስ-አንቷን ሺሴኬዲ አደራዳሪነት ዋና ከተማዪቱ ኪንሻሳ ላይ ትናንት ተጀምሮ የነበረው የኢትዮጵያ፣ የሱዳንና የግብፅ ድርድር ያለስኬት ተበተነ።

ስለጉዳዩ ዛሬ የተጠየቁት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱያሪች “ልዩነቶችን የማቻቻልንና የመተባበርን አስፈላጊነት በበቂ ሁኔታ ላጎላው አልችልም” ብለዋል።

የተጨበጠ ስምምነት ላይ ለመድረስ ወገኖቹ አበርትተው መጣራቸውን እንዲቀጥሉ የመንግሥታቱ ድርጅት ጥሪ እንደሚያደግ ዱያሪች አመልክተው በወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነታቸው ወገኖቹን እንደገና ለማገናኘት ፕሬዚዳንት ሺሴኬዲ ስላደረጉት ጥረት አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

የወገኖቹን ጥረቶች ለመደገፍም የመንግሥታቱ ድርጅት አሁንም ዝግጁ መሆኑን በድጋሚ እንደሚያረጋግጥ አስታውቀው “እኔ ይህንን ልተው፤ አንተም ይህንን ተው” የማለት አካሄድና የትብብርን አስፈላጊነት በድጋሚ አንስተው አሳስበዋል።

ለድርድሩ መስተጓጎል “ከኢትዮጵያ በኩል በቅንነት ለመነጋገር የፖለቲካ ፍላጎት የለም” ሲል የግብፅ ወገን መክሰሱን ስለሁኔታው ዋና ፀሃፊው ምን እንደሚያስቡና በጉዳዩ ውስጥ ዲፕሎማሲ ሊጫወት የሚችለው ሚና ይኖር እንደሆነ እንዲያብራሩ ለዱያሪች ጥያቄውን ያነሳው ጋዜጠኛ ጠቁሟል።

እስካሁን ከየትኛውም ወገን በይፋ የወጣ መግለጫ የለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ስምምነት ላይ ሳይደረስ ኢትዮጵያ ወደ ሁለተኛው ሙሌት ብትገባ “ሊገመት የማይችል ትርምስ በአካባቢው ይፈጠራል” ሲሉ የግብፅ ፕሬዚዳንት ባለፈው ሣምንት መዛታቸውን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ግድቡን በመሙላት ካልቀጠለች “ከተቋራጩ ኩባንያ ጋር በገባችው ውል መሠረት የአንድ ቢሊዮን ዶላር ኪሣራ እንደሚደርስባት” ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በቅርቡ አሳውቀው ነበር።

የኅዳሴ ግድብ ግንባታ መሠረት የተጣለበትን አሥረኛ ዓመት አስመልክቶ ከአምስት ቀናት በፊት በትዊተር ገፃቸው ላይ መልዕክት ያሰፈሩት የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ የሆኑት የውኃ፣ የመስኖና የኤሌክትሪክ ኃይል ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ የግድቡ ግንባታ 79 ከመቶ መጠናቀቁን ገልፀው “ኢትዮጵያ ተፋሰሱን ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ በሆነ መልኩ በጋራ ለመጠቀም አቋሟ የማይናወፅ ነው” ብለዋል።

የህዳሴ ድርድር ኪንሻ ላይ ተጀመረ

የህዳሴ ድርድር ኪንሻ ላይ ተጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:26 0:00

ዩናይትድ ስቴትስ በኅዳሴው ግድብ ጉዳይ

ፎቶ ፋይል፦ የህዳሴ ግድብ

ኢትዮጵያ ግብጽ እና ሱዳን የታላቁ ኅዳሴ ግድብን በተመለከተ ያላቸውን አለመግባባት በትብብር እና ገንቢ በሆነ ጥረት እንዲፈቱ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ መስጠቷን እንደምትቀጥል አስታውቃለች።

ሦስቱ ሃገሮች ውጤታማ ወደሆነ ውይይት እንዲመለሱ እናበረታታለን ሲል የዋይት ሃውስ የብሄራዊ ጸጥታ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ቢሮ አስታውቋል።

ውዝግቡ ገንቢ መፍትሄ እንዲያገኝ እና በክልሉ ያለው ውጥረት እንዲረግብ ለመርዳት በምንሰጠው ድጋፍ ከግድቡ ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ሚዛናዊ በሆነ መንገድ መያዛቸውን በማረጋገጥ መስራታችንን እንቀጥላለን ብሏል መግለጫው።

የኢትዮጵያ እና ሱዳን ውጥረት አይሏል

የኢትዮጵያ እና ሱዳን ውጥረት አይሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:13 0:00

ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG