በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 93 በመቶ መድረሱን ኢትዮጵያ አስታወቀች


የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 93 በመቶ መድረሱን ኢትዮጵያ አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:39 0:00

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ 93 በመቶ መድረሱን ኢትዮጵያ አስታወቀች

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታ ሒደት፣ 93 በመቶ መድረሱን፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ አስታወቁ፡፡

የግድቡ “አራተኛው ዙር ሙሌት” እንደተጠናቀቀ፣ ባለፈው ሳምንት እሑድ ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ግድቡ የያዘው የውኃ መጠንም፣ 42 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትርመድረሱን፣ ትላንት በመንግሥት ብዙኀን መገናኛዎች በተሰራጨ ዝግጅት ላይ ተናግረዋል፡፡

የግድቡ ግንባታ እና የውኃ ሙሌት የቀጠለው፣ ግብጽ፣ ሙሌቱ፥ ከተፋሰሱ ሀገራት የመርሖዎች ስምምነት ውጭ እየተካሔደ እንደሚገኝ እየገለጸች ባለችበት ወቅት ነው፡፡

ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባል እናበዐዲስ አበባዩኒቨርሲቲ የሃይድሮፖለቲክስ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ በበኩላቸው፣ሙሌቱ የመርሖዎች ስምምነቱን እንዳልጣሰ አስረድተዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG