በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕዳሴ ግድብ ውይይት በአራት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መሪዎቹ አስታወቁ


የሕዳሴ ግድብ ውይይት በአራት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መሪዎቹ አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:24 0:00

የሕዳሴ ግድብ ውይይት በአራት ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መሪዎቹ አስታወቁ

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ስምምነትን፣ በአራት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እንደሚሠሩ፣ የኢትዮጵያ እና የግብፅ መሪዎች እንዳስታወቁ ሮይተርስ ዘግቧል።

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ቡድን አባል ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ፣ ይህ የሮይተርስ ዜና ከመሰማቱ አስቀድሞ በሰጡን አስተያየት፣ “ድርድሩ ረዘም ያለ ጊዜ ሊወስድ እንደሚችል” አመልክተዋል፡፡

የውኃ ሙሌቱ፣ ከግድቡ የግንባታ ሒደት ጋራ በተጣጣመ መልኩ እንደሚከናወን የገለጹት ፕር. ይልማ፣ የክረምቱ መራዘም፣ ግድቡ ኃይል ማመንጨት መጀመሩ እና ከፍታው መጨመሩ፣ በሚያዘውና በሚለቀቀው የውኃ መጠን ላይ ሚና እንዳላቸው አስረድተዋል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታሕ አል-ሲሲ፣ ካይሮ ላይ ተገናኝተው፣ በኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ስላለው የሕዳሴ ግድብ የውኃ አሞላል እና በሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የሚኖረውን የአጠቃቀም ደንብ በተመለከተ፣ ሱዳንን ጨምሮ በሦስቱ አገሮች መካከል ሲደረግ የነበረውንና የተቋረጠውን ድርድር በአራት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ ተስማምተዋል።

የሮይተርስ ዜና ወኪል፣ በሁለቱ ሀገራት መካከል የወጣውን የጋራ መግለጫ ጠቅሶ እንደዘገበው፣ ሁለቱ መሪዎች፣ ስምምነቱን በአራት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተስማማተዋል፤ ተብሏል።

የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደል ፈታሕ አል-ሲሲ፣ ትላንት ረቡዕ፣ ካይሮ ላይ ተገናኝተው፣ በኢትዮጵያ በመገንባት ላይ ስላለው የሕዳሴ ግድብ፣ እንዲሁም በሱዳን በተፈጠረው ቀውስ ላይ እንደተነጋገሩ፣ የግብጹ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት አስታውቋል።

አል-ሲሲ፣ ዐቢይ አሕመድን በቤተ መንግሥታቸው ተቀብለው ማነጋገራቸውን ጽ/ቤቱ ጨምሮ ገልጿል።ሁለቱ መሪዎች ካይሮ ላይ የተገናኙት፣ በአል-ሲሲ አስተናጋጅነት፣ ስድስት የሱዳን ጎረቤት ሀገራት፣ ለ12 ሳምንታት የዘለቀውን የሱዳን ግጭት አስመልክቶ ለመነጋገር፣ ካይሮ ላይ ካደረጉት ስብሰባ ጎን ለጎን ነው።

ሙሉ ዘገባን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG