በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሀመር በኅዳሴ ጉዳይ አውሮፓ ናቸው


የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር
የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር

የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር በዚህ ሳምንት ወደ ስቶክሆልም እና ብራስልስ ተጉዘው በኅዳሴ ግድብ እና እንዲሁም ኢትዮጵያ እና ሱዳን ውስጥ እየተካሄዱ ባሉት ግጭቶች ዙሪያ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የስቶክሆልሙ ዓለም አቀፍ የውሃ ጉዳይ ተቋም በሚያስተናግደው የዓለም የውሃ ሳምንት ጉባዔ ላይ የሚካፈሉት አምባሳደር ማይክ የስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም እና ምርምር ተቋም በሚያስተናግደው ውይይት ላይም እንደሚካፈሉ ተመልክቷል፡፡

ሀመር የታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዋናው የዩናይትድ ስቴትስ መልዕክተኛ እንደመሆናቸው የውሃ አያያዝ፣ አጠቃቀም እና ተደራሽነትነት የሚመለከቱ ሥምምነቶች ለአፍሪካ ቀንድ ጸጥታ እና መረጋጋት ሊያበረክቱ ስለሚችሉት አስተዋጻኦ እንደሚወያዩ ተገልጿል፡፡ በመቀጠል ወደብረሰልስ በማቅናት ኢትዮጵያን እና ሱዳንን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከአውሮፓ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡

አምባሳደር ሀመር በኢትዮጵያ ጉዳይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች ያሉትን ግጭቶች በውይይት ለመፍታት ዩናይትድ ስቴትስ እና የአውሮፓ ሕብረት እንዴት ሊደግፉ እንደሚችሉ፤ በተጨማሪም ለሰላማዊ ዜጎች በሚደረግ ጥበቃ አስፈላጊነት ዙሪያም እንደሚወያዩ ተገልጧል።

ልዩ መልዕክተኛው ከአውሮፓ ሕብረት ባለሥልጣናት ጋር ሚያደርጓቸው ውይይቶች የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ለማስቆም ምክኒያት የሆነው ሥምምነት በተሟላ መልኩ እንዲተገበር እና በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን በሙሉ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሰላም፣ ፍትህ እና ተጠያቂነትን ለማስፈን በሚሰጡት ድጋፍ ዙሪያም ይመክራሉ ተብሏል።

አምባሳደር ሀመር በሱዳኑ ግጭት የአፈሙዞች ላንቃ እንዲዘጋ፤ ተጠያቂነትን ለማስከበር እና ዲሞክራሲያዊ የሲቪል አስተዳደር ወደ ቀድሞ ቦታው ለመመለስ የተያዙ አህጉራዊ እና አለምአቀፋዊ ጥረቶች ዙሪያም ይወያያሉ። ለክልሉ የሚሰጠውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማጠናከር የተያዘው ሥራ ማቀላጠፉ እንደሚቀጥልም መግለጫው ጠቅሷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG