በቅርቡ ከኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስቱሪ ሚኒስትርነት ኃላፊነታቸው የተነሱት የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር “ከሥልጣን የተነሳሁት ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ አልቀላቀል በማለቱ በተወሰደ ዕርምጃ ነው” ይላሉ።
በአማራ ክልል አዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ጃዊ ወረዳ ፈንድቃ ከተማ ጣና በለስ የስኳር ልማት ፕሮጀክ ሰራተኞች እሁድ ዕለት ጥቃት ተፈፅሞ ሦስት ሰዎች ከተገደሉና ሌላ አንድ ሰው ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰ የክልሉ መንግሥትና ለደኅንነታቸው የሰጉ ምስክሮች ተናገሩ።
በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ በመንግሥት በተጠራ የወጣቶች ኮንፈረንስ ላይ ለተገኙ ተሣታፊዎች ይከፈላል ከተባለ የውሎ አበል ክፍያ ጋር በተያያዘ የተፈጠረ አለመግባባት ወደ ፖሊስና ወጣቶች ግጭት አምርቶ በአንድ ወጣት ላይ ከባድ ድብደባ እንደፈፀመ፤ በሁለት የፖሊስ አባላት ላይም ጉዳት እንደደረሰ ታውቋል።
ንብረታቸው በመቃጠሉ ሳቢይም ከቆቦ ከተማ ሸሽተው አላማጣ መግባታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ባለፈው ሳምንት በጎንደር ከተማ በተቀሰቀው ቀውስና ብጥብጥ በርካታ የንግድ ድርጅቶች መውደማቸውን መንግስትና የከተማው ነዋሪዎች ገለጹ።
ማክሰኞለት የተባበሩት መንግስታት የመብት አጣሪ ቡድን የኤርትራ ባለስልጣናት በዜጎቻቸው ላይ እየፈጸሙ ነው ያላቸውን ሰፊ የመብት ጥሰቶች፤ አስረድቶ የኤርትራ መሪዎች በዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት ወይንም በሌሎች የፍትህ ችሎቶች ክስ እንዲመሰረትባቸው መጠየቁ ይታወሳል።
የአረና ትግራይ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዓንዶም ገብረሥላሴ እና የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዘነበ ሲሳይ በዛሬው ዕለት ጠዋት በፓርቲው ፅ/ቤት የሚገኙ የቆዩ ሰነዶችና ቆሻሻ በማቃጠል ላይ እያሉ በልዩ ኃይል ፖሊሶች ታግተው በመቀሌ ከተማ ውስጥ ለአምስት ስዓታት ታሥረው መቆየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።
ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት 32 ሰዎች አንደኛው አቶ ሀብታይ ገብረን አነጋግረናል። አቶ ሀብታይ እንዴት እንደተጠለፉና ኋላም እንዴት ወደ ሃገራቸው እንደተመለሱ በዝርዝር አብራርተዋል። የጠለፏቸውም የአርቦች ግንቦት ሰባት ሰዎች እንደሆኑ አቶ ሀብታይ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣኖችንና የግንቦት ሰባት ተወካዮችን ስለጉዳዩ ለማነጋገር ሞክረን አልተሳካልንም።
ኤርትራ ያለው ዴምህት በሚል አህጽሮት የሚታወቀው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ እንቅስቃሴ የተባለው ድርጅት ስለጠለፋው የማውቀው ነገር የለም ብሏል።
በደቡብ ሱዳን ሁለት ስቴቶች ወይም ክልሎች ውስጥ በተቀሰቀሰ ከባድ ውጊያና በረሃብ ምክንያት ከመቶ ሺህ በላይ ደቡብ ሱዳናዊያን ባለፉ ሁለት ወራት ውስጥ መፈናቀላቸውንና መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር አስታውቋል፡፡