በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ኤርትራ ተጠልፈው የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንደተመለሱ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ


የኤርትራ ካርታ
የኤርትራ ካርታ

ወደ ሀገራቸው ከተመለሱት 32 ሰዎች አንደኛው አቶ ሀብታይ ገብረን አነጋግረናል። አቶ ሀብታይ እንዴት እንደተጠለፉና ኋላም እንዴት ወደ ሃገራቸው እንደተመለሱ በዝርዝር አብራርተዋል። የጠለፏቸውም የአርቦች ግንቦት ሰባት ሰዎች እንደሆኑ አቶ ሀብታይ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣኖችንና የግንቦት ሰባት ተወካዮችን ስለጉዳዩ ለማነጋገር ሞክረን አልተሳካልንም።

ተጠልፈው ወደ ኤርትራ ተወስደው እንደነበር የገለጹት አቶ ሀብታይ ገብረ እንዴት እንደተጠለፉና ኋላም እንዴት ወደ ሃግራቸው እንደተመለሱ ያብራራሉ።

“መጀመርያ ወደ ወርቅ ፍለጋ ስራ ነበር የሄድነው። ጥር 27 ቀን ከንጋቱ 12 ሰአት ላይ ነበር የመጡት። ከዚያም እኛ ተደናገጥንና በአራት ማዕዝናት ተኩስ ከፈቱ። አንዳንዶቻችን ተያዝን ሌሎች ደግሞ አመለጡ። ቦታው ግርማይ መንገድ ይባላል። ከዚያም አንድ ላይ ሰብስበው ተሻገሩ ብለው ተከዘ ወንዝ ውስጥ አስገቡን። እኛ ዋና አንችልምና እንዴት እንሻገራለን ስንላቸው ለምንድነው የማትችሉት? ግቡ ብለው በማስገደድ ይደብደቡን ጀመር። 34 ነበርን ገባን።" ብሏል።

አክለውም፣ "አስገድደው የወሰዱን ሰዎች ታጣቂዎች ናቸው። የአርበኛ ግንቦት ሰባት ነን አሉ። ሆኖም ሌሎች የኤርትራ መንግስት ሰዎችም ነበሩባቸው የሚል ግምት አለን። የወሰዱን ሰዎች አማርኛ ተናጋሪዎች ናቸው። ጥቂት ትግርኛ ተናጋሪዎችም ነበሩባቸው። ከ 34 ታችን አንደኛው ስለታመመ መለሱት። ሌሎቹ ደግሞ አባትና ልጅ ስለነበሩ አስር ቤተሰባችንን ጥለን ልንሄድ ነው ወይ? ሲሉ ልጁን ወስደው አባትየውን መለሷቸውና 32 ታችንን ወሰዱን።”

የኤርትራ ካርታ
የኤርትራ ካርታ

ያኔ የተወሰድንበትን ቦታ ለይተን ባናውቀውም ራቅ ያለ ነበር ይላሉ አቶ ሀብታይ ገብረ።

“ቦተውን ለይተን አናውቀውም ግን ራቅ ያለ ነበር። ለአራት ሰአታት ያህል ከተጓዝን በኋላ አንድ ቦታ ላይ ወሃ አጠጡን። ከዚያም ለስምንት ሰአታትት ያህል ከተጓዝን በኋላ በመኪና ወደ ሰፈራቸው ወስደው እዛው አሳደሩን። በነገታው የነሱን አይነት አፈርማ ካኪ አልብሰው በመኪና ወደ ጎልጅ ከዚያም ወደ ተሰነይ ወሰዱን። ከተሰነይ ትልቅ መስኖ ወዳለብት ቦታ ወሰዱን።”

ትልቅ መስኖ ባለበት ቦታ ላይ አርበኞቹ ትልቅ የእርሻ ቦታ እንዳላቸውና በኤርትራ ምድር ያለውን ቦታ ተከራይተነው ነው እንደሚሉ አቶ ሀብታይ ገልጸው እኛ ግን የማን እንደሆነ አናውቅም ብለዋል። እዛ ምን ይሰሩ እንደነበርም ገልጸዋል።

“እዛ ላይ ብዙ ስራ ነው የነበረው። በርበሬና ባምያ መልቀም፣ ጤፍ ማጨድ፣ በቆሎ መላጥና በእጅ መፈልፈል የመሳሰሉትን ነግሮች ካለረፍት እንሰራ ነበር። ወደዚህ እስከተመለስንበት ጊዜ ድረስ።”

ለውትድርና ሊያሰልጠኗችሁ አልሞከሩም ወይ ለሚለው ጥያቄ አቶ ሀብታይ ገብረ አዎን ይጠቃቅሱ ነበር ብለዋል።

“ለማምለጥ ከሞከራችሁ እዚችው ትቆይዋታላችሁ። ጠባይ ካሳመራችሁ ግን በአጭር ጊዜ ወታደራዊ ስልጣን ታደርጋላችሁ ይሉን ነበር።”

አቶ ሀብታይ ገብረ በመጨረሻም መቼና እንዴት ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ አብራርተዋል።

“የተመለስነው የካቲት 19 ቀን ነው ከቀኑ ሰባት ሰአት ድረስ ስራ ውለን ከዚያም ምሳ በልተን አረፍ እንዲሉን ምንም አይነት ኢንፎርሜሽን ሳይሰጡን መኪና ላይ ተሳፈሩ አሉን። እኛም ግራ ገብቶን የት ነው የምንሄደው ያለነው በሚል ጭንቀት ውስጥ ገብተን ነበር። ጎልጅ አከባቢ ስንደርስ በሌላ መኪና አሳፈሩን። ከዛም ገጠር አከባቢ እንደደረስን የኤርትራ ሃላፊዎችና የአርበኛ ሃላፊ ተረቡን። የአርበኞቹ ሃላፊ መዐዛው ጌጤ ይባልላ። የኤርትራው መንግሥት ደግሞ ሻምበል ዳዊት ነው የሚሉት። የኤርትራው ሃላፊ መጀመርያ ከመኪና እንደወረድን ተሰልፉ ብሎ አሰለፈን። ከዚያም ኢትዮጵያውያን ናችሁ? ብሎ ጠየቀን። አዎን አልን። ሁላችሁም መጣችሁ ወይ ብሎ ጠየቀን አዎን አለን። ከዚያም በናንተ ላይ የተፈጸምው ተግባር የኤርትራ መንግሥት የማያውቀው ነገር አይደለም። የኤርትራ መንግሥት ስለጉዳዩ እንደሰማ ስለናንተ ጉዳይ ሲነጋግር ቆይቷል። አሁን ወደ ሀገራችሁ ትመለሳላችሁ አለን።”

አቶ መአዛው ጌጤም በአማርኛ እንደተናገሩ አቶ ሀብታይ ጠቁሟል።

“መአዛው ጌጤም በአማርኛ ተናገረ። ስህተት ነበር የተሰራው በዛ ምልክ መሰራት የለበትምና አሁን ወደ ሀገራችሁ ትመለሳላችሁ አለን። ከዚያም ማታ በመኪና ወደ ኡምኒ ሐጀር ወሰዱን። እዣ አድረን ሌሊት 10 ሰአት ላይ ሱድን ግዛት ውስጥ ወደሚገኘው ሃንዳይት ሸኝተው ለቀቁንና የሱዳን ሰራዊት ተረከቡን። መንነታችንን ከጠየቁ በኋኣ ወደ ሱዳን መንግስት መስርያ ቤት ወሰዱን። ከዚያም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተነጋገሩ መሰለኝ በጀልብ አሸጋገሩን የኛዎቹ ተቀበሉን።”

በአሁኑ ወቅት ከኤርትራ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት ሰዎች ሑመራ እንደሚገኙ አቶ ሀብታይ ገብሩ ገልጸዋል።

አቶ ሀብታይን ያነጋገረው ባልደረባችን ገብረ ገብረመድኅን ሲሆን አዳነች ፍሰሀየ ታቀርበዋለች።

ወደ ኤርትራ ተጠልፈው የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንደተመለሱ የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG