በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአረና አመራር አባላት ታሥረው ተፈቱ


የአረና ትግራይ አርማ
የአረና ትግራይ አርማ

የአረና ትግራይ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዓንዶም ገብረሥላሴ እና የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዘነበ ሲሳይ በዛሬው ዕለት ጠዋት በፓርቲው ፅ/ቤት የሚገኙ የቆዩ ሰነዶችና ቆሻሻ በማቃጠል ላይ እያሉ በልዩ ኃይል ፖሊሶች ታግተው በመቀሌ ከተማ ውስጥ ለአምስት ስዓታት ታሥረው መቆየታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የአረና ትግራይ ሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ዓንዶም ገብረሥላሴ እና የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ዘነበ ሲሳይ ዛሪ ጠዋት አምስት ሰዓት አካባቢ መቀሌ ከሚገኘው ጽ/ቤታቸው የቆዩ ሰነዶችን ለማስወገድ ራቅ ያለ ቦታ ሄደው በማቃጠል ላይ እያሉ በልዩ ኃይል ፖሊስ ለአምስት ሰዓታት ያህል መታሠራቸውንና መታገዳቸውን ይናገራሉ።

እንደታሰሩበት የገለጹት ፖሊስ ፅ/ቤት በበኩሉ የታሠረም ይሁን የተያዘ ሰው የለም ብሏል።

ፋይል ፎቶ - የትግራይ ክልል
ፋይል ፎቶ - የትግራይ ክልል

ለእገታው በምክንያትነት የተገለፀላቸውም “ለማቃጠል ማን ፈቀደላችሁ?” የሚል እንደሆነ አቶ ዓንዶም ገልፀው “ማንም ሰው ከአደጋ ተጠንቀቆ ወረቀቶችንም ሆነ ቆሻሻ ነገሮችን ማቃጠል ይችላል” ይላሉ።

የትግርኛ ዝግጅት ክፍል ባልደረባችን ገብረ ገብረመድኅን አቶ አንዶምን አነጋግሯል ጽዮን ግርማ እንዲህ አጠናቅራዋለች። ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምፅ ያድምጡ።

የአረና አመራር አባላት ታሥረው ተፈቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:53 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ


XS
SM
MD
LG