በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ከሥልጣን የተነሳሁት ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ አልቀላቀል በማለቱ በተወሰደ ዕርምጃ ነው” ወ/ሮ ፈትለወርቅ


ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር

በቅርቡ ከኢትዮጵያ ንግድና ኢንዱስቱሪ ሚኒስትርነት ኃላፊነታቸው የተነሱት የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር “ከሥልጣን የተነሳሁት ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ አልቀላቀል በማለቱ በተወሰደ ዕርምጃ ነው” ይላሉ።

ባለው ሳምንት ቪኦኤ ያነጋገራቸው የብልፅግና ፓርቲ ቃል አቀባይ አቶ አወሉ አብዲ በበኩላቸው ሚኒስትሯ ከሥልጣናቸው የተነሱት “በሥራ አፈጻፀም ጉድለት፣ ሆን ብሎ ህዝባዊ አገልግሎቶችን በማደናቀፍ እና እንዲሁም ባሳዩት የሥራ ድክመት ነው” ብለዋል።

ወ/ሮ ፈትለወርቅ አባባሉ ከሃቅ የራቀ ነው፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁን በካቢኔው እንዲሁም በፓርላማ ይህን የመሰለ ግምገማ ቀርቦ አያውቅም” ሲሉ ይሟገታሉ። ብልፅግና ፓርቲ ትክክለኛ ምክንያቱን ለመሸፋፈን ያለው ነው” ሲሉም ይወነጅላሉ።

የትግርኛ ክፍል ባልደረባችን ገብረ ገብረመድህን በዚህና በህወሓትና በፌዴራል መንግሥቱ መካከል እየተካረረ ባለው የፖለቲካ ውጥረት ዙሪያ አነጋግሯቸዋል።

የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

“ከሥልጣን የተነሳሁት ህወሓት ከብልፅግና ፓርቲ አልቀላቀል በማለቱ በተወሰደ ዕርምጃ ነው” ወ/ሮ ፈትለወርቅ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:57 0:00


የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG