በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተባብሶ ቀጥሏል ስለሚባለው የትግራይ ፆታዊ ጥቃት


ፎቶ ፋይል፦ እዳጋ ሓሙስ፤ መቀሌ፤ የካቲት 2013 ዓ.ም.
ፎቶ ፋይል፦ እዳጋ ሓሙስ፤ መቀሌ፤ የካቲት 2013 ዓ.ም.

ትግራይ ውስጥ የመደፈር ጥቃት የተፈፀመባቸው ሴቶችና ልጃገረዶች ቁጥር ከአንድ ሺህ አራት መቶ መብለጡን የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

የክልሉ የፍትህ ቢሮና የሴቶች ጉዳይ ቢሮዎች ባለሥልጣናት “በኤርትራና በኢትዮጵያ ወታደሮች እየተፈፀመ ነው” ያሉት ጥቃት “በቁጥርም በጭካኔ አድራጎትም ተባብሶ እንደቀጠለ” ተናግረዋል።

ከተፈፀመባቸው የመድፈር ጥቃት በተጨማሪ በአካሎቻቸው ላይ አሲድ መርጨትን ጨምሮ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 527 ሴቶችና ልጃገረዶች መኖራቸውን ከዓይደር ሆስፒታል የተገኘ መረጃ ያሳያል።

በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የተደረገ ቢያንስ አምስት ተጠርጣሪዎች መኖራቸውን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ የጠቆመ ሲሆን በመድፈር በተጠረጠሩ 25 ወታደሮች ላይ ክሥ መመሥረቱንና በሦስት ወታደሮች ላይ የጥፋተኛነት ብይን መተላለፉን የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታውቋል።

ከኤርትራ መንግሥት አስተያየት ለማግኘት ያደረገው ጥረት አለመሳካቱን ገልፆ የትግርኛ ዝግጅት ክፍል ባልደረባችን ገብረ ገብረመድህን ያጠናቀረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሃየ ታቀርበዋለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ተባብሶ ቀጥሏል ስለሚባለው የትግራይ ፆታዊ ጥቃት
please wait

No media source currently available

0:00 0:12:38 0:00


XS
SM
MD
LG