ባለፈው ቅዳሜ ሶማልያ ዋና ከተማ ሞቅዲሾ ውስጥ የደረሰው ፍንዳታ፣ በሀገሪቱ የሽብር ታሪክ ከፍተኛው መሆኑ ተገለፀ። ነዋሪዎች በጥቃቱ የተሰማቸውን ቁጣ ለመግለፅ፣ ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውም ታውቋል፣ ዩናይትድ ስቴትስም ጥቃቱን ማውገዛ ታውቋል። በቅዳሜው ጥቃት የሞቱት ሰዎች ቁጥር 276 መድረሱን፣ የቆሰሉት ደግሞ 429 እንደሆኑ የማስታወቂያ ሚኒስትሩ አብድራህማን ኦስማን ገልፀዋል፡፡
የትነበርሽ ንጉሤ ለአካል ጉዳተኞች መብት መሟገት የጀመረችው በዩኒቨርስቲ የሕግ ትምህርቷን በመከታተል ላይ በነበረችበት ወቅት ነው፡፡ በዩኒቨርስቲ አስተዳደር ውስጥ እርሷን ጨምሮ፣ ለአይነ ስውራን ተማሪዎች፣ የብሬይል መጽሕፍ እንዲዘጋጅ አስተዋፅዖ አድርጋለች፡፡
ሰሞኑን ከሦስት ሺህ በላይ ፍልሰተኞች ሊቢያ ውስጥ መያዛቸው ተጠቆመ፡፡ ፍልሰተኞቹ በባለፈው ቅዳሜ በሊቢያዋ ሰበርታ ከተማ ዳርቻ አካባቢ ሲሆን የተያዙት በህገወጥ አሸጋጋሪዎች አማካኝነት ወደ አውሮፓ ለመጓዝ በዝግጅት ላይ የነበሩ ናቸው፡፡ ፍልሰተኞቹ ወደ እስር ቤት መወሰዳቸውም ተጠቁሟል፡፡
"ወይኔ ግርማ የኦምሓጀር ልጅ፣ ሊብያ ሆነ ኑሮዬ፡፡ እናት ለዓለም አንድ ነች፣ ለእኔ ግን ዓለሜ ነች፡፡" * በሰሜን ሊብያ ዛዊያ እስር ቤት ግድግዳ ላይ የተፃፈ፡፡
የ2010 ዓ.ም. የእሬቻ በዓል በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ በደማቅ ስነ ስርዓት ተከብሯል፡፡
ለሮሒንግያ ፍልሰተኞች የሚደረገው የእርድታ አቅርቦት ጥሪ ቀጥሏል፣ በአሁኑ ወቅት ወደ ባንግላዴሽ የሚሰደዱ የፍልሰተኞች ቁጥር ከአቅም በላይ እንደሆነም ባለሥልጣናት እየተናገሩ ናቸው። ሰሜን ራከሄን የሚኖሩና ቁጥራቸው ያልታወቀ ሙስሊሞች ደግሞ በድንበር በኩል እየተሰደዱ መሆናቸው ታውቋል። የተመድ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ዓለማቀፍ ድርጅቶችም በተለያዩ አካባቢዎች ተሰማርተው፣ በስደት ላይ ሆነው የተጎዱትን ለመርዳት እየሞከሩ መሆናቸው ታውቋል።
የመስቀል ደመራ በዓል በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ማምሻውን በደማቅ ሥነ ስርዓት ተከብሯል፡፡
በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ሥፍራዎች በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ የሞቱትም የተፈናቀሉት ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር እየተጣራ እንደሆነ የመንግሥት ጉዳዮች ፅ/ቤት ሚኒስትር ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ አስታወቁ፡፡ ዛሬ ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለፁት አሁን ያለው የፀጥታ ሁኔታ ፈፅሞ ከግጭት የነፃ እንዳልሆነና አንዳንድ የታጠቁ ኃይሎችም ፀጥታውን ለማደፍረስ እንደሚንቀሳቀሱ ነው የተናገሩ፡፡ የእሬቻ በዓል በሰላም እንዲከበርም በቂ ዝግጅት እንደተከናወነ፣ ገልፀዋል፡፡
የሲሊከን ቫሊ ታሪክና ወጣ ገባውን ለማየት፣ በዛው ያሉ አፍሪካውያን ቴክኖሎጂስቶችንና የሥራ ፈጣሪዎችን ለማግኘት እና ለማነጋገር ወደ ካሊፎርኒያ ሳንፍራንሲስኮ የተጓዘው ሰሎሞን አባተ በተለያዩ የሞያ ዘርፎች የተሰማሩ ኢትዮጵያውያንን አግኝቶ አነጋገሯል፡፡ ለዛሬ ከፕሮፌሰር አዱኛው ወርቁ ጋር በሙዚቃ፣ በቤተሠብ፣ በሥራ፣ በሀገር ጉዳይ የመሳሰሉት ጉዳዬችን አንሰተው ተጨዋውተዋል፡፡
ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ገጣሚ ሰዓዳ ሙሐመድ፣ በጋዜጠኝነት ዓለም በሕትመት ሚዲያዎች እፎይታ፣ ዕለታዊ አዲስ፣ አዲስ አድማስ ጋዜጦች ላይ በከፍተኛና በዋና አዘጋጅነት፣ በሪፖርተርነት፣ በአምደኝነት ሰርታለች፡፡
ወደ 3መቶ 80 ሺሕ የሚጠጉ ሮሒንግያ ሙስሊሞች ከምዕራብ ሚያንማር እየሸሹ መውጣት ዩናይትድ ስቴትስ ከሀገሪቱ የወታደራዊ የበላይነት ከሰፈነበት መንግሥት ጋር ያላትን ግንኙነት በአዲስ መልክ እንድታይ አነሳስቷታል። ይህ ሰብዓዊ ቀውስ ዋሺንግተን ከአንጋፋዋ የዲሞክራሲ ታጋይ አንግ ሳን ሱቺ ጋር ያላትን ቅርብ ግንኙነት እየጎዳ ነው ሲል የአሜሪካ ድምፅ ዘጋቢ ቢል ጋሎ ባጠናቀረው ዘገባ ጠቅሷል።
ፍልሰተኞቹ የሜዲትራንያንን ባህር በጀልባ በማቋረጥ ወደ አውሮፓ ለመጓዝ ዝግጅት ላይ የነበሩ ሲሆን በፈቃደኝነት ላይ በተመሰረተ ወደ ሃገራቸው መልሷቸዋል፡፡ የሜዲትራኒያንን ባህር በሟቋረጥ አውሮፓ ለመድረስ ሙከራ ለማድረግ ይጠባበቁ የነበሩ ሲሆኑ በሊቢያ የመጠለያ ጣቢያዎች የማስቀመጥና በቂ ማቆያ ስፍራ ባለመኖሩ በተለይም በበጋ ወቅት አስቸጋሪ መሆኑን ሮይተርስ ገልጿል፡፡
ምዕራባዊ ሚያንማር ውስጥ በተቀሰቀሰውና ወደ 4መቶ ሺህ የበሮሒንግያ ሙስሊሞች፣ ድንበር አቋርጠው ወደ ባንግላዴሽ እንዲሰደዱ ያስገደደውን ቀውስ በተመለከተ፣ የተመድ የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በዚህ ሳምንት ውስጥ አንድ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያካሂድ ተገለጸ።
ሜክሲኮ ውስጥ ትናንት ማታ በደረሰ ርዕደ ምድር፤ ቢያንስ አሥራ ስድስት ሰዎች መሞታቸው፣ ይህም ከ100 ዓመታት በላይ በሆነው በአገሪቱ የመሬት ነውጥ ታሪክ ከፍተኛው መሆኑን፣ ፕሬዚደንቱ አስታወቁ። በሬክተር መለኪያ 8.2 የተመዘገበው ይህ ነውጥ፣ ቱናላ ከተባለችው ከተማ 100 ኪሎ ርቀት ላይ ነው፣ የሜክሲኮን ደቡባዊ ፓሲፊክ ውቅያኖስ ወደብ ትናንት ሌሊቱን የመታው።
ሀሪኬን፣ ኃይለኛ ዝናብ ቀላቅሎ የሚነፍሰውና ኢርማ ተብሎ የተሰየመው ይህ አውሎ ነፋስ፣ ዛሬ ዐርብ አብዛኛውን የኩባ ምሥራቃዊ ክፍል እንደመታና በምዕራብ በኩል ወደ ሰሜናዊ ምዕራብ ተጉዞ፣ የባሀማስን ክፍል እንደሚያዳርስ፣ ብሔራዊው የሀሪኬን ማዕከል አስታወቀ። ኢርማ በዛሬው ዕለት፣ ከ5ኛ ደረጃ ከፍ ብሎ፣ ኃይለኛ ወደሚባለው ደረጃ አራት እንደደረሰ የገለፀው ማዕከሉ፣ በቀጣዮቹ ቀናት በተጠናከረ መልኩ የፍሎሪዳን ግዛት እንደሚያዳርስ፣ የአየር ትንበያ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገሮች የተወሰኑ ፍልሰተኞችን፣ ስደተኞች እና ጥገኝነት ፈላጊዎች እንዲቀበሉ የተመደበውን ኮታ እንዲያከብሩ የህብረቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ብይን ሰጠ። የአውሮፓ ፍትህ ፍርድ ቤት ሃንጋሪና ስሎቫኪያ የኮታ ምደባውን በመቃወም ያቀረቡትን ክስ ውድቅ አድርጎባቸዋል።
“አይአርኤምኤ” የሚል ቅጽል ስም የተሰጠው ብርቱ ዝናብ የተቀላቀለበት ከባድ አውሎ ነፋስ ዛሬ ማለዳ ላይ የካሪባያን ደሴቶችን ማትራመስ ቀጥሏል። ሀይለኛው ነፋስ፣ ካባድ ማዕበልና አደገኛው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ እያደረሱ ናቸው። ሀይለኛ ዝናብን አዝሎ በሰአት 295 ኪሎ ሜትር የሚወነጨፈው ከባድ አውሎ ነፋስ ሴት ማርቲንን እና አንጉኢላን እያተራመሰ ነው። አደገኛው ሁሪኪን በከፊል ቨርጂን ደሴቶችም በኩል ያልፋል ተብሏል።
ዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች የምግብ ዋስትናቸውን እንዲያረጋግጡና ከድኅነት እንዲወጡ ለማገዝ ለጀመረችው “የፊድ ዘ ፊውቸር ፕሮግራም” ለሁለተኛ ዙር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የመረጠቻቸውን ሀገራት ይፋ አደረገች፡፡
በጣሊያን ሮም የኖሩ የነበሩ ከ800 በላይ ኤርትራዊያን እና ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የኖሩበት ከነበረበት ሕንፃ እንዲወጡ በፓሊስ ሲገደዱ ግጭት ተፈጥሯል፡፡ እአአ ከ2013 ጀምሮ ይኖሩበት ከነበረ ሕንፃ እንዲወጡ ሲገደዱ ከመካከላቸው ነፍሰጡር ሴቶች፣ ሕፃናት እንደሚገኙበት አሶሼትድ ፕሬስ ገልጿል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ