በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ገጣሚ ሰዓዳ ሙሐመድ ትጣራለች


እሾሃማ ወርቅ
እሾሃማ ወርቅ

ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ገጣሚ ሰዓዳ ሙሐመድ፣ በጋዜጠኝነት ዓለም በሕትመት ሚዲያዎች እፎይታ፣ ዕለታዊ አዲስ፣ አዲስ አድማስ ጋዜጦች ላይ በከፍተኛና በዋና አዘጋጅነት፣ በሪፖርተርነት፣ በአምደኝነት ሰርታለች፡፡

ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ገጣሚ ሰዓዳ ሙሐመድ፣ በጋዜጠኝነት ዓለም በሕትመት ሚዲያዎች እፎይታ፣ ዕለታዊ አዲስ፣ አዲስ አድማስ ጋዜጦች ላይ በከፍተኛና በዋና አዘጋጅነት፣ በሪፖርተርነት፣ በአምደኝነት ሰርታለች፡፡

በእፍታ መጽሐፍ አጫጭር ልቦለዶቿ እና ግጥሞቿም ለሕትመት በቅተዋል፡፡ ፖፑሌሽንና ሚዲያ ሴንተር በተከታታይ ባሳተማቸው መድብሎችም ላይ ሥራዎቿ ተካተዋል። በሀገር ፍቅር ቴአትርና በፑሽኪን የሥነ ፅሁፍ መድረኮች ላይ የግጥም ሥራዎቿን ታቀርብ ነበር፡፡

በኢትዮጵያ ራድዮ "ከመጽሐፍት ዓለም" ፕሮግራም ለንባብ የበቃው "እሾሃማ ወርቅ" መጽሐፋዋም፣ በዓረብ ሀገር ለስራ በተጓዘችበት ወቅት በዓረብ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ላይ ተመርኩዛ ኑሮቸውን በጥብበ ሥራዋ አሳይታለች፡።

በ1990ዎቹ በኢትዮጵያ ራድዮ የቅዳሜ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ የተለያዩ ድራማዎችን፣ አጫጭር ትረካዎችንም ትፅፍ ነበር፡፡

ከሌሎች ደራሲያን ጋር በቅንጅትም የቴሌቪዥንና የራድዮ ድራማዎችን ትጽፍ ነበር፡፡

የቀን ቅኝት፣ የቤት ሥራየመሳሰሉ ሥራዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ጋዜጠኛ፣ ገጣሚ ሰአዳ ሙሐመድ ሰሞኑን በኩላሊት ህመም በጠና ታማለች፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ገጣሚ ሰዓዳ ሙሐመድ ትጣራለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:03 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG