ሥጋት ውስጥ የወደቀው የግብፅ እስላማዊ ሕግ ዋናው ተቋም አል አዛር ዩኒቨርስቲ እስላማዊ ግዛት አልቃይዳና ሌሎች ነውጠኛ ቡድኖች ለሚከተሉት አምፅ አቀንቃኝ፣ እስላምና ዘመናዊ ለዘብተኛ ገፅታ ለመስጠት እየሠራ ነው፡፡
በፈረንሳይ ወደብ በካሌ የስደተኞች መኖሪያ አካባቢ በአፍጋኒዎችና አፍሪካውያን መካከል በተፈጠረ ውዝግብ ከ20 በላይ የሚሆኑ ቆስለዋል፡፡
በፈረንሳይ ወደብ በካሌ የስደተኞች መኖሪያ አካባቢ በአፍጋኒዎችና አፍሪካውያን መካከል በተፈጠረ ውዝግብ ከ20 በላይ የሚሆኑ ቆስለዋል፡፡ 2መቶ የሚሆኑ ስደተኞች ከትናት በስቲያ ሰኞ ጀምሮ እስከ ትናንት ማክሰኞ ማምሻውን በዘለቀ ግጭት በርካቶች ሲጎዱ የተወሰኑ ስደተኞች ስለትነት ያላቸው የብረት ዕቃዎችን እና እንጨቶችን ይዘው ነበር፡፡ በሀምሌ መጀመሪያ በኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን መካከል ግጭቶች ተከስቶ አሥራ ስድስት ስዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
በሰሜናዊው ስፔን ካዲዝ ከአፍሪካ ሀገራት በሦስት ጀልባዎች እና በሰባት በአነስተኛ(የስፖርት መወዳደሪያ) ጀልባዎች በመጫን ወደ ስፔን ባሕር አቋርጠው መጓዛቸው ተጠቆመ፡፡ ሥድስቱ ጀልባዎች የተጫኑት 283 ከሰሜን አፍሪካ እና 34ቱ ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገሮች የመጡ መሆናቸው ሲገለፅ ከእነሱም ውስጥ ሴቶችና ሕፃናት ይገኙበታል፡፡
የኢትዮጵያ ጥንታዊ ከተማ የሆነችው ሐረር በ7ኛው ክ/ዘ ስትቆረቆር የእስልምና ባህል ማዕከል ተብላ ትጠራለች፡፡ “ጀጎል” ተብሎ በሚጠራዉ ግንብ የተከበበችው ሐረር ከተማ አምስት በሮች አሏት፡፡ ሐረር ከተማ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት /ዩኔስኮ/ ዓለምቀፍ ቅርስነት ተመዝግባለች፡፡
ለኢትዮጵያ ቱሪዝም እንቅስቃሴ መጠንሰስ እና መጎልበት ግንባር ቀደሙን ሚና የተጫዎቱት አቶ ኃብተ ሥላሴ ታፈሰ የቀብር ሥነ ሥርዓት ትናንት በመንበረ ፀባዎት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል፡፡
ሰሜን ኮርያ የዩናይትድ ስቴትስ የፓሲፊክ ግዛት በሆነው ጉዋም ላይ የሚሳይል ጥቃት ለመክፈት “በጥንቃቄ እየመረመርኩ ነው” ስትል ዛሬ በመናገርዋ በዩናይትድ ስቴትስና በሰሜን ኮርያ መካከል ወታደራዊ ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚለው ስጋት መባባሱ ቀጥሏል። ሰሜን ኮርያ ይህን ምላሽ የሰጠችው የአሜርካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩናይትድ ስቴትስ ላይ የሚሰነዘር ማንኛውም ዓይነት ዛቻ “የእሳትና የቁጣ ምላሽ ያገኛል” የሚል ዛቻ ካሰሙ ሰዓታት በኋል ነው።
ዩናይትድ ስቴትስ የስደተኛ ማስፈር መርሃ ግብሯ አማካኝነት አምጥታ ለምታሰፍራቸው ስደተኞች የመጀመሪያው የሦሥት ወር ጊዜ መኖሪያ ቤት እና ሥራ እንዲያገኙ፣ የአሜሪካን አኗኗርና ባህል ለማስተዋወቅ ብዙ ርብርብ የሚጠይቅ ጊዜ ነው። በርግጥ በአሜሪካ ማኀበረሠብ ውስጥ በደምብ ተዋሕዶ መኖር እንዲህ በሦሥት ወር ውስጥ የሚያልቅ አይደለም።
ዩናይትድ ስቴትስ ከፊሊፒንስ፣ ከታይላንድ እና ከማሌዥያ ጋር ባሏት የኢኮኖሚና የፀጥታ ትብብር ጉዳዮች ላይ ለመምከር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ሬክስ ቲለርሰን ወደዚያው ተጉዘዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የአሁኑ ጉዞ ዋና አጀንዳ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል የሰሜን ኮሪያ የኒኩሌር ጦር መሣሪያ መርኃግብር ከዋና ዋናዎቹ የመነጋገሪያ ነጥቦች አንዱ ነው።
የኢትዮጵያ ፓርላማ ባለፈው ዓመት በመላ ሀገሪቱ ላይ የጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጀ አንስቷል፡፡ አዋጁ የተጣለው በሀገሪቱ ውስጥ ለወራት የዘለቁ የአመፅ እንቅስቃሴዎች ከተስፋፉ በኋላ ነው፡፡
ናዋሪነታቸው ኦስሎ ኖርዌይ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ ተስፋማርያም “የፊደል እንቆቅልሽ” በአራት የተለያዩ ቋንቋዎች በማዘጋጀት በተለያዩ ሀገራት ለማከፋፈል በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ይገለፃሉ፡፡ በስቱዱዮዋችን በመገኘት ሥራዎቻቸውን በተመለከተ ቃለ መጠይቅ አድርገዋል፡፡
ሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተሰጠውን ተጨማሪ የአንድ ወር የእፎይታ ጊዜ እንዲጠቀሙና ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል፡፡
የኢትዮጵያን የሠብዓዊ መብት ይዞታና አጠቃላይ አስተዳድር ከዩናይትድ ስቴይትስ ፖሊሲ ጋር ለመቃነት ያለመ ረቂቅ ሕግ በዛሬ ዕለት በሕግ አርቃቂው የኮንግረስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፊት ቀርቦ፤ ድምፅ እንዲሰጥበት ሙሉ በሙሉ ስምምነት ተደረሶበታል።
አንዲት ስኒ ቡና! አቦል ካለበለዚያም እስከ በረካው - የብዙ ሰው ሱስና የለት ተለት ቀጠሮው ነው። በተለይ በጠዋት “ፉት” የተባለች እንደሁ አህ!!! መልካም ቀን ተጀመረ ማለት ነው… አንድ ሰሞኑን የወጣ አዲስ የጥናት ሪፖርት ደግሞ “ምን ቀን ብቻ? ዕድሜ ሙሉ እንጂ!” ይላል። በቀን ሦስት ስኒ ቡና የሚያጣጥሙ ሰዎች ከማይጠጡቱ ለተሻለ የዘመን ርዝማኔ እንዲሁ እንዳጣጣሙት ይኖራሉ፡፡
"ማንኛዋም የአፍሪካ ሴት ልጅ ስታድግ መሪ የመሆን ብቃት አላት” ሲሉ የማላዊ የቀድሞ ፕሬዚደንት ጆይስ ባንዳ ተናገሩ። ሴት ልጅ ለመሪነት ስትበቃ የምትሰራውን በሚገባ የምትውቅ ትሆናለች ሲሉ አክለዋል። ጆይስ ባንድ ይህን የተናገሩት የመሪነት ብቃት ያላቸውን ሴቶች ሁሉ ካሉበት ተፈልገው እንዲገኙ፣ ስልጠና እንዲያገኙ፣ ማኅበረሠቦቻቸው ውስጥ የበለጠ ንቁ ሚና እንዲጫወቱ ለማድረግ የሚጠቅሙ መንገዶችን ይፋ ባደረጉበት ሥነ ሥርዓት ላይ ነው።
የሐረር ከተማ ታሪካዊና ጥንታዊ ከመሆኗ በተጨማሪ በርካታ ቱሪስቶች የሚጎርፉባት ምሥራቃዊ የኢትዮጵያ ክፍል ናት፡፡ ጎብኝዎች ከሚማረኩባቸው ተፈጥሮዊ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶች በተጨማሪ የሐረር ጅቦች ልማዳነት ብዙዎችን የሚያስደምም ሆኖ ይገኛል::
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ጄ. ትረምፕ የበኩር ልጅ ዶናልድ ትረምፕ (ትንሹ) የሩሲያ መንግሥት ባለሥልጣን ናቸው ብሎ አምኖባቸው ከነበረ አንዲት ግለሰብ ጋር የሂላሪ ክሊንተንን የፕሬዚዳንትነት ፉክክር ሊጎዳ ይችላል ተብሎ የታሰበ መረጃ ስለማግኘት ለመነጋገር ተገናኝቶ እንደነበረ የወጡ መረጃዎችን የሚያጠናክሩ የኢሜል ልውውጦችን ይፋ አድርጓል፡፡
በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንትዶናልድ ትራምፕ በሀምቡርግ ጀርመን የጂ-20 መሪዎች ጉባዔ ላይ መገኘታቸውን ተክትሎ በእርሳቸው ኃላፊነት የቤተሰባቸው አባላት ጣልቃ ገብነት እንደመነጋገሪያ ርዕስ እንደገና ትኩረት ስቧል፡፡ የቪኦኤ የዋይት ኃውስ ዋና ዘጋቢ ስቴቨን ኸርማን እንደሚለው ለዚህ ትኩረት ምክንያት የሆነው የፕሬዚዳንት ሴት ልጅ ኢቫንካ ትራምፕ በአንደኛው የመሪዎቹ ሥራ ጉባዔ ላይ ስለተገኘች ነው፡፡
34ኛው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያኖች ስፖርትና ባህል ፌደሬሽን ዝግጅት፣ በሲያትል ዋሺንግተን የኢትዮጵያውያን ቀን አከባበር የተለያዩ ዝግጅቶች ተስተናግደዋል፡፡
ከተማሪ መምህር እና የጥበብ ሰው ጋር የተያዘ ወግ! አሉላ ከበደ እና ሱራፌል ወንድሙ (ፀሐፊ ተውኔት፣ ዳይሬክተር እና ገጣሚ )
ተጨማሪ ይጫኑ