ዩናይትድ ስቴይትስ በኢትዮጵያ ለተከሰተው ድርቅ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት ተጨማሪ 268 ሚሊዮን
ዶላርስ እርዳታ ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት እንደሚያስፈልግና የአስቸኳይ ጊዜ መልስ ሰጭ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ልትልክ እንደሆነ የUSAID አስተዳዳሪ ጌል ስሚስ አስታወቁ። እርዳታው ዩናይትድ ስቴይስ አስቀድማ ከሰጠችው 500 ሚሊዮን ዶላርስ ተጨማሪ እንደሆነም ተገልጿል።
በዛሬውለት ይፋ የምናደርገው እርዳታ ለሌሎች ለጋሽ ሀገሮችም ምሳሌ የሚሆን ስልት ነው።የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (USAID) አስተዳዳሪ ጌል ስሚስ
“ኤል ኒኞ” የሚባለው የአየር ጸባይ ለውጥ ብዙ አካባቢዎችን እያወከ ይገኛል። በደቡባዊ አፍሪካ እየከፋ ሄዷል በላቲን አሜሪካም ጉዳት አድርሷል፤ እንደ ኢትዮጵያ ግን የበረታበት ስፍራ የለም ብለዋል የዩናይትድ ስቴይትስ ዓለም አቀፍ እርዳታ ድርጅት USAID ዋና ስራ አስኪያጅ ጊል ስሚት። ይህ አሃዝ የዩናይትድ ስቴይትስ መንግስት እስካሁን ያበረከተችውን 500 ሚሊዮን ዶላርስ እርዳታ የሚያካትት አይደለም።
“በዛሬውለት ይፋ የምናደርገው እርዳታ ለሌሎች ለጋሽ ሀገሮችም ምሳሌ የሚሆን ስልት ነው። ይሄም የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ሰራተኞች ቡድን ወደ ኢትዮጵያ ማሰማራት ነው። እስካሁን ያለውን አጣዳፊ ስራ የሚያስተባበሩና የሚያሳልጡ ባለሙያዎችን ያካትታል ቡድኑ” ብለዋል የUSAID አስተዳዳሪ ጌል ስሚስ።
እርዳታው ዩናይትድ ስቴይስ አስቀድማ ከሰጠችው 500 ሚሊዮን ዶላርስ ተጨማሪ እንደሆነም ተገልጿል።