በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል የተወሰደዉ የሃይል እርምጃ ስህተት መሆኑን ባለስልጣናት አዉቀዋል ሲሉ ሁለት የዩናትድ ስቴትስ (United States) ከፍተኛ ባለስልጣናት አዲስ አበባ ዉስጥ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናገሩ።
በዩናትድ ስቴትስ (United States) ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ (USAID) ዳይሬክተር ጌል ስሚዝ (Gale Smith) እና የዩናትድ ስቴትስ (United States) የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ (Linda Thomas-Greenfield) ለጋዜጠኞች እንዳብራሩት በኦሮሚያ ክልል በተፈጠረዉ ሁኔታ ምክንያት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የሰፋ ሰለመሆኑም ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር የጋራ መግባባት አለ።
እስክንድር ፍሬዉ ተከታዮን ዘግቧል ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።
የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናቱ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ሃያ ስድስተኛ ጉባዔ በአዲስ አበባ ውስጥ ለመሳተፍ ነው የተጓዙት። የጉባዔውን ፎቶ መድብሎች ለመመልከት ከዚህ በታች ያለውን መድብል ይጫኑ።